






በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዞቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት አስተባባሪነት በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ በቦንጋ ከተማ ክልላዊ ማጠቃለያ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ስራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ፕላን ቢሮ ምክትል ኃላፊ (ዶ/ር )ፈለቀች ተክለማርያም እንዳሉት ባለፋት የለውጥ ዓመታት ሴቶችን ማኅበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ገፅታ የቀየረ ዕምርታዊ ድሎች የተመዘገበበት መሆኑን ገልጸዋል።
ብልጽግና ፓርቲ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል እድሎችንና ድሎችን ይዞ የመጣ፣ ሴቶችን በኢኮኖሚ በማብቃት በኩል የሚታዩና የሚቆጠሩ ውጤቶች መመዝገቡን አንስተዋል።
ይህንን እድሎችና ድሎችን ይበልጥ አስጠብቆ ለማስቀጠል ተማህበረሰቡ ደማቅ አሻራ ለማኖር በየደረጃው ያለው የሴቶች ሊግ አባላት ግንባር ቀደም ሚናቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል ።
ከመላ ሴቶች ጋር ሰፊ ንቅናቄ በማድረግ በብልፅግና መሪነት የሚካሄደው ሀገራዊ የለውጥ ጉዞን ሴቶች በሚገባ ተረድተው የሂደቱ ንቁ ተሳታፊና ተዋናይ እንዲሆኑ ለማስቻል መድረኩ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል ።
በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው መድረክ በሀገር ደረጃ ከ 8 ሚሊዮን በላይ ሴቶች ተሳታፊ መሆናቸውንም አክለው ገለጸዋል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተሳካ እንዲሆን ከወዲሁ ሴቶች በፓርቲያቸው የስኬት ጉዞዎች ዙርያ በቂ ግንዛቤን በመጨበጥ ለቀጣይ ተልዕኮዎች ራሳቸውን እንዲያዘጋጁና እንደ ሀገር በሚከናወኑ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያስችል መድረክ እንደሆነም አመላክተዋል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ሰላማዊ ነጻ ፍትሀዊኒ ተዓማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅና ሴቶች በምርጫዉ ሂደት የበኩላቸውን እንዲወጡ ያለመ አስገንዝበዋል ።
መድረኩ ሴቶችን ለማብቃትና ተሳትፎአቸውን ለማረጋገጥ ቃል የምንገባበት ወቅት መሆኑን ገልጸዋል።
የካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አጥፉ ኃይሌ ባደረጉት መክፈቻ ንግግር የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራት ተከናውኗል ።
ከለውጡ በኃላ አካታችነት በተግባር በመግለጥ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፍ ላይ ተጨበጥጭ ውጤቶች ማስመዝገብ መቻሉን ጠቁመዋል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ፣ነጻ ፣ፍትሐዊና ተዓማኒነት ያለው ምርጫ ሆኖ እንዲጠናቀቅና የፓርቲያችን መንትያ ግቦችን ለማሳካት ሴቶች የመሪነነት ሚናቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል ።
በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ !!” በሚል መሪ ሀሳብተዘጋጀው ሰነድ ላይ የክልለ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰብለጸጋ አየለ ቀርቦ ውይይት እነተደረገበት ይገኛል።
