የአፍሪካ ቡና ንግድ ዓውደ ርዕይ ከጥር 27 እስከ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ይካሄዳል

የአፍሪካ ቡና ንግድ ዓውደ ርዕይ ከጥር 27 እስከ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ይካሄዳል
ለ22ኛ ጊዜ የሚካሄደው ዐውደ ርዕዩ የአፍሪካ ቡና ኢንዱስትሪ እድገትን ለማጠናከር እና በዘርፉ ዓለም አቀፍ የንግድ ትስስርን መፍጠር እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያ በ2024 መርሐ ግብሩን ያስተናገደች ሲሆን፥ መንግስት አሁን ላይ ለዘርፉ የሰጠው ከፍተኛ ትኩረት በድጋሚ ለማስተናገድ እንድትመረጥ ማስቻሉ ተጠቅሷል፡፡
መድረኩ በአፍሪካ ልዩ ጣዕም ያላቸው ቡናዎችን በማስተዋወቅ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነታቸውን ለማሳደግ እንደሚያግዝም ተጠቁሟል፡፡
በመድረኩ ከተለያዩ አፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ የቡና አምራቾችና ላኪዎችን ጨምሮ ከ2 ሺህ በላይ የዘርፉ ተዋንያን እንደሚሳተፉ ይጠበቃል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል፡፡
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
በሊንክደን
