አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በመፍጠር ወደ ዘርፉ እንዲቀላቀሉ ከማድረግ እና ነባር ኢንዱስትሪዎችን ከማጠናከር ረገድ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው-አቶ ግዛው ጋግያብ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ እና ኢኖቬሽን ቢሮ በክልሉ ከሚገኙ የየዞን መምሪያ ሀላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት ጋር የ2017 ዓም ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ላይ በቴፒ ከተማ ውይይት ተካሂዷል።
በመድረኩ የ2017 ዓም ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ በበሮው ልማት ዕቅድ ዳይሬክተር በሆኑት አቶ አንዱዓለም ሽፈራው ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በመድረኩ የቢሮው ሃላፊ አቶ ግዛው ጋግያብ እንደገለፁት፣በ2017ዓ.ም አዳዲስ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ዘርፉ እንዲቀላቀሉ ለማድረግ በማቀድ በአነስተኛ 80 በመካከለኛ 9 በድምሩ 89 ኢንዱስትሪዎችን ማቋቋም ተችሏል።
ነባር አነስተኛ እና መካከለኛ የማንፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችን ከማጠናከር አንጻር በአነስተኛ 179 እና በመካከለኛ 29 በድምሩ 208 የማንፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችን ማጠናከር መቻሉንና አዲስ በተቋቋሙ እና ነባር በተጠናከሩ ኢንዱስትሪዎች ለ4,864 ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን ጠቅሰው በቀጣይ ለተሻለ ውጤት በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ብለዋል።
አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ወደ ኢንዱስትሪ እንዲሸጋገሩ ማድረግ፣በገጠር ኢንዱስትሪን ማስፋፋት ፣ኢንተርፕራይዞችን መደገፍና ማጠናከር እንዲሁም ቴክኖሎጂዎችን ለተጠቃሚው የማሸጋገር ስራውን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ያሉት የቢሮው ምክትል እና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ብርቅነሽ ሻንቆ ናቸው።


አክለውም፣የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች የደረጃ ሽግግር ማሳደግ፣ የሊዝ ፋይናንስ መጠቀም ፣የገበያ ትስስር መፍጠር ፣የአምራች ኢንተርፕራይዞችን የተኪ ምርት መጠንና ጥራት ማሳደግ ላይ በትኩረት በመስራት ከዘርፉ ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባ አብራርተዋል።
የቢሮው ምክትል እና የኢኖቬሽን ዘርፍ ሀላፊ አቶ ምትኩ አስፋው በበኩላቸው፣የአግልግሎት አሰጣጥን በዘላቂነት ለማሻሻልና ቀልጣፋ ለማድረግ የሚሰጡ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ የታገዙ መሆን እንደሚገባቸው በመግለፅ ይህን እውን ለማድረግ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክህሎትና ግንዛቤ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል።
ለተገልጋዩ ማህበረሰብ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እና የተቋማትን የመረጃ ልውውጥ ውጤታማነት ለማረጋገጥ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በክልሉ ካሉ ቢሮዎች እና ሌሎች በዘርፉ ከተሰማሩት ባለድርሻ አካላት ጋር ለመሥራት በሚያስችሉ የትኩረት ነጥቦች ላይ ውይይት በማድረግ ከስምምነት የተደረሰ ሲሆን የ2018 በጀት ዓመት ዋና ዋና ተግባራት ግቦች ውል ስምምነት ፈርማ መርሐ ግብርም ተከናውኗል።
በመድረኩ ላይ ከክልሉ ሁሉም ዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮች የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በካሳሁን አሰፋ
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
