




የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የክልል፣የዞንና የወረዳዉ ከፍተኛ አመራሮች የሆስፒታሉ ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው ተመልክቷል።
የገዋታ ወረዳ የቆንዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ አፈጻጸም አሁን ላይ 98 ከመቶ መድረሱን በጉብኝቱ ወቅት በተደረገው ገለጻ ማረጋገጥ ተችሏል።
የሆስፒታሉ ቀሪ ሥራዎች ተጠናቆ አስፈላጊ ግብዓቶች ተሟልቶላቸው ለአገልግሎት ሲበቃ ለአራት ወረዳዎች አገልግሎት መስጠት የሚችል ነዉ።
በጉብኝቱ የሆስፒታሉ ግንባታ ቀሪ ሥራዎችን በመፋጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለአገልግሎት እንዲበቃ ርዕሰ መስተዳድሩ መመሪያ ተሰጥቷል።
በጉብኝቱ ርዕሰ መስተዳድር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግበብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ፣ አስተባባሪ አካላትን ጨምሮ ሌሎች የክልል፣የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።
በፍቅር ከበደ
