



የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) በካፋ ዞን ሳይለም ወረዳ ተቺቢ ቀበሌ በ31 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባውን የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ መርቀዉ አገልግሎት አስጀምረዋል።
የንጹህ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት ግንባታ በሰኔ 30/2014 ዓ.ም እንደተጀመረና 31 ሚሊዮን ብር ወጪ የወጣበት ሲሆን ከ3ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።
ፕሮጀክት ግንባታዉ የጉድጓድ ቁፋሮና ግንባታ፣ባለ100 ሜትር ኪየቭ የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከር፣ 1.2 ኪ/ሜ ዋና የግፊት መስመር ቱቦ አቅርቦትና ዝርጋታ፣ 7.4 ኪሎ ሜትር ማሰራጫ መሰመር አቅርቦትና ዝርጋታ፣8 ባለአራት ፎሰት የውሃ መኖ ግንባታ፣ 3 ባለስምንት ፎሰት የተማሪዎች እጅ መታጠቢያ፣የፓምፕና ጄኔሬተር አቅርቦትና ተከላ፣የጥበቃ ቤት ግንባታ እና የተለያዩ የቧንቧ መሸከሚያ እንዲሁም ቻምበር ቦክስ ግንባታና ሌሎችን ያካተተ መሆኑን የክልሉ ዉሃ፣ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ መረጃ ያመለክታል።
በተያያዘም ዜና ርዕሰ መስተዳድሩ በካፋ ዞን ሳይለም ወረዳ በህብረተሰብ ተሳትፎ የተሰራ 6 ኪሎ ሜትር ቆሪ-ተቺቢ የመንገድ ልማት ሥራን መርቀዉ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል።
በምረቃዉ ሥነ ሥርዓት ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ የክልል፣ዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የአከባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በፍቅር ከበደ
