የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት አፈጻጸምን በተመለከተ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ ጋር ምክክር አደረገ፡፡

Spread the love

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ነጻ፣ ተዓማኒና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈላጊውን የጊዜ ሠሌዳ በማዘጋጀት ከክልሎች ጋር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ያሉበትን ደረጃ እየገመገመ ይገኛል፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብስቢ አቶ ተስፋዬ ንዋይ እና ሌሎች የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈጻሚ አካላት በደቡብ ምዕራብ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ተገኝተው ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጋር የጋራ ምክክር አድርገዋል፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ንዋይ በክልሉ ለምርጫ አስቻይ የሆኑ ቅደመ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆናቸውን በመጥቀስ ቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት በተለይም የመራጮችና የዕጩዎች ምዝገባ፣ የምርጫ ጣቢያና የምርጫ ክልል የምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላና መረጣ ሂደት፣ የቅሬታና አቤቱታ አቀራረብና አፈታት ሂደት ማሳላጥ የሚያስችሉ አሠራሮችን ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡

የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ለማከናወን ጊዜያዊ የጊዜ ሠሌዳ የተዘጋጀ መሆኑን በመጥቀስ የዘንድሮ ምርጫ ካላፉት ጊዜያት በተሻለ መንገድ በቴክኖሎጂ በታገዘ መንገድ የሚከናወንና ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ምቹ የሆኑ አማራጭ የዕጩዎችና የመራጮች ምዝገባ መንገዶችን ይዞ የቀረበ መሆኑ አንስተዋል፡፡

ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩም በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ለምርጫ አስቻይ ሁኔታዎች መኖራቸውን ገልጸው ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በበርካታ ጉዳዮች በቅርበት እየሠሩ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡ በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነጻነት የሚሳተፉበት ፕሮግራሞቻቸውን ለመራጮች የሚያቀርቡበት ምቹ የፖለቲካና የጸጥታ ሥነ ምህዳር መኖሩንም ገልጸዋል፡፡

በክልሉ በኩልም 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የተሳካና በሁሉም ዘንድ ቅቡልነት ያለው እንዲሆን ከመንግሥት የሚጠብቀበትን ኃላፊነት ለመወጣት ቁርጠኛ መሆናቸውንም አንሰተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *