የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያን ለሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር አስጎብኝተናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Spread the love

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በተቀበሉበት ወቅት፣ የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እና ፓርክን በጋራ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ፤ ለጥቁር ሕዝቦች ነፃነት ትግል ውድ ዋጋ ለከፈሉ ጀግኖች መታሰቢያ በተገነባው ሐውልት ሥር የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ አክለውም፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ እና በውቧ መዲና አዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ፣ ጊዜያቸው ፍሬያማ እንዲሆን በራሳቸውና በከተማ አስተዳደሩ ስም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ኢቢሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *