የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የዋቻ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

Spread the love

በ2018 ሩብ ዓመት የከተማውን ማኅብረሰብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ዘርፈብዙ ተግባራት መከናወናቸውን በካፋ ዞን፣ የዋቻ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ሁነኛው ታደሰ ከክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ በበጀት ዓመቱ በከተማው ማኅበራዊ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ተግባራት ተከናውኗል ብለዋል።

የውስጥ ገቢ የመሰብሰብ አቅም በማሳደግ ለኅብረተሰቡ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በተሰጠው ትኩረት በበጀት ዓመቱ ከማዘጋጃ ቤታዊ አግልግሎት ለመሰብሰብ ከታቀደው ውስጥ 84 ከመቶ ማሳከት መቻሉን ከንቲባ ሁነኛው ገልጸዋል።

በተሰበሰበው ገቢም በከተማው በርካታ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ሥራዎች እየተከናወነ መኾኑን በመጠቆም፣ ከእነዚህም ውስጥ፥ የ20 ኪሎሜትር የውስጥ ለውጥ መንገድ ከፈታ፣ ጠጠር የማልበስ፣ የውሃና መብራት ተደራሽነት ማስፋት ተችሏል ብለዋል አቶ ሁነኛው።

ከተሞች ለኑሮ ምቹና ፅዱ እንዲኾኑ ለማስቻል ተግባራዊ የኾነውን የፅዱ ኢትዮጵያ ኢንሼቲቭ በመከተል በከተማው ደረጃውን የጠበቀ የመጸዳጃና መታጠቢያ ህንጻ ተገንብተው ለአገልግሎት መብቃቱን ነው ኃላፊው ያስረዱት።

በመንግሥት ተቋማት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የሚነሳውን ቅሬታ በመሠረታዊነት በመፍታት፣ ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በተሰጠው ትኩረት ለውጥ እየተመዘገበ መኾኑንም አቶ ሁነኛው ጨምሮ ገልጸዋል።

በከተማው የመሬት ሀብት በአግባቡ የመለየት የማስተዳደር እንዲሁም የምዝገባና የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እየተሰጠ እንደሚገኝ ነው የከተማ አስተዳደሩ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ስራአስኪያጅ አቶ ሽመለስ አስራት የገለጹት።

በከተማው የመሬት ሀብትን በአግባቡ ለማስተዳደር እንዲረዳ የዲጂታል አሰራር መዘርጋቱን የጠቆሙት አቶ ሽመልስ በዚህም ከ3ሺህ 550 በላይ ይዞታዎች ፋይል ወደ ሲስተም መግባቱን አስረድተዋል።

ይህም በቀደሙት ጊዜያት ከመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች ጋር የሚነሱ የአግልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በተሻለ መልኩ በመቅረፈ የተገልጋይ እርካታን እያሳደገ ይገኛል ብለዋል።

በከተማው የይዞታ ምዝገባ ስራው በተሻለ መልኩ እየተከናወነ እንደሚገኝ ያስረዱት አቶ ሽመለስ በዚህም በ5 መንደሮች የልየታ ስራ በመጠናቀቁ ባለይዞታዎች ፋይል ይዘው በመቅረብ የመሬት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እየወሰዱ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *