የሚዛን አማን ከተማን በመልሶ ማልማት ለነዋሪው ምቹና ተመራጭ ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎች በልዩ ትኩረት እየተሰሩ መሆኑን የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ

Spread the love

የመልሶ ማልማት ስራ የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ከሌሎች ከተሞች ጋር ተወዳደሪ የሚያደርጋት መሆኑን የከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

በከተማው ካነጋገርናቸው ነዋሪዎች መካከል አቶ አሳምነው መንግስቴ እና ወ/ሮ ትሁን ታደሰ እየተከናወነ ያለው የሚዛን አማን ከተማ መልሶ መልማት ስራ ለከተማ እድገት ወሳኝ መሆኑንና በዚህም አካባቢው እየለወጠ መሆኑን በርካታ ለውጦች እየተመዘገበ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ይህም የከተማው ማህበረሰብ የተሻለ ገቢ እንዲያገኝና የከተማዋን ኢኮኖሚ አቅም ከማሳደግ አንፃር ፋይዳው የጎላ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

የሚዘን አማን ከተማ ማዘጋጀ ቤት መሬት ዝግጅትና መልሶ ማልማት ቡድን መሪ አቶ ታምሩ ወዛብ በበኩላቸው የከተማ መልሶ ማልማት ሥራውን ውጤታማ ለማደረግ ከማህበረሰቡና ከከተማ ነዋሪዎች ጋር በመወያየት ወደተግባር በመገባቱ ውጤታማና በተሻለ መልኩ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመልሶ ማልማት ከተማዋን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ከፍ ያለ ነው ያሉት አቶ ታምሩ በዚሁ ዓመት በሚዛንና አማን 63 ቤቶች ወደ መልሶ ማልማት እንዲገነቡና 3 ሄክታር የከተማ መሬት በመልሶ ማልማት ወደ ስራ በማስገባት ለነዋሪው ምቹ ከተማን ለመፍጠር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

የሚዛን አማን ከተማ ማዘጋጃ ቤት የመሬት ልማት ማነጅመንት ዘርፍ ኃላፊ እና ምክትል ከንቲባ አቶ ብሩክ ሰለሞን፤ የከተማው መልሶ ማልማት ተግባር የደቀቁ ቤቶች ህንፃ የማቀድ፣ የመገንባትና ከተማዋን ኢኮኖሚ እንዲነቃቃ የማድረግ ስራ በሰፊው እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የመልሶ ማልማት ስራ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በመከናወን ላይ እንደሚገኝና የደቀቁ እና ያረጁ ቤቶችን በከተማ ልማት እሳቤ ወደ ልማት በማስገባት ለከተማው ኢኮኖሚ መመንጨት እንዲችል በማድረግ በየአመቱ በርካታ መሻሻሎች በማሳየት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህም ተግባር ዘንድሮ ከወትሮው በተለየ መልኩ በሚዛን 18 ባላይዞታዎች አንድ የሚያደርግ በኩታ ገጠም ኮምፕሌክስ ህንፃ እንዲገነቡ እና በአማን 24 ባላይዞታዎች በመልሶ ማልማት እንዲገቡ ውል የማስገባት ስራ እየተከናወ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አሁን ላይ የሚዛን አማን ከተማ መልሶ መልማት ስራ ጥሩ መልክ መያዙን የገለጹት አቶ ብሩክ ለዚህም የከተማው ማህበረሰብ ድጋፍና የክልሉ መንግሥት የጀመረው ክትትል ማጠናከር እንዳለበት አንስተዋል፡፡

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *