“በጓሮ አትክልትና በፍራፍሬ ልማት ተጠቃሚ ነን” – በዳውሮ ዞን የከጪ ወረዳ አርሶ-አደሮች

Spread the love

በበጋ መስኖ የተለያዩ የጓሮ አትክልቶችን እና ፍራፍሬዎችን በማልማት ተጠቃሚነታቸውን እያሳደጉ መምጣታቸውን በዳውሮ ዞን ከጪ ወረዳ የከጪ ቱታ ቀበሌ አርሶ-አደሮች ገለጹ።

ከ1 ሺህ ሄክታር በላይ መሬትን በተለያዩ ሰብሎች በማልማት ከ285 ሺህ በላይ ኩንታል ምርት ለማግኘት እየሰራ መሆኑን የወረዳው ግብርና፣ አከባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ልማት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የከጪ ወረዳ በተለያየ ምቹ አየር ፀባይ ያላት ሰትሆን ፤ በዘንድሮ በበጋ መስኖ ስራ የተሻለ ምርት እንደሚጠበቅ የጽህፈት ቤቱ መረጃ ያመለክታል።

አርሶ-አደሮቹ አቶ ተስፋዬ ኃይሌ፣ አቶ ተሻለ ተስፋዬና አቶ ዱባለ ታደሰ በከጪ ቱታ ቀበሌ ዩኒ መስኖ በባህላዊ መንገድ ውሃ በመጥለፍ የተለያዩ የጓሮ አትክልቶችንና ፍራፍሬ እያለሙ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ጥቅል ጎመን፣ ቀይ ስር፣ ቆስጣ፣ ነጭ ሽንኩርትና ካሮት እንዲሁም በዚሁ አከባቢ ወደ የቡና ችግኝ በማፍላት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከጪ ወረዳ ግብርና፣ አከባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ልማት ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ታምራት ሀዳሮ ፤ በዘንድሮ የበጋ መስኖ ስራ የተሻለ ምርት ለማግኘት ከሌላው ጊዜ በተለየ አቅደው በጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ፣ በበጋ ስንዴ በተለይም ለእንሰት ምርት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።

ደ.ሬ.ቴ.ድ. እንደዘገበው ፤ በወረዳው በበጋ መስኖ፣ ጓሮ አትክልቶችና ፍራፍሬ እንዲሁም በበጋ ስንዴ ልማት ከ285 ሺህ 240 ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *