ጫካ ከገቡ የታጣቂ ቡድኖች ጋር ችግሩን በሰላማዊ መንገድ በአጭር ጊዜ ለመፍታት መንግስት እየሰራ እንደሆነ ገልጿል ፡፡ በዚህም ተጨባች ውጤት እየተመዘገበ ነው፡፡ ሆኖም ከችግሩ ውስብስብነት አንጻር አሁንም በአማራና ኦሮሚያ ክልል ከችግሩ ያለተላቀቁ አካባዎች አሉ፡፡ ችግሩን ከስር መሰረቱ ለመፍታት ምን እየተሰሩ ነው ፤

Spread the love

👉እንደሀገር የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነትን ከመከላከል አኳያ መንግስት እየሰራ ያለው ስራ አበረታች ነው፤ የመንግስት የስድስት ወር አፈጻጸም ላይ ባለፈው 2016 ዓ.ም የዋጋ ግሽበት 23 ነጥብ 7 በመቶ የነበረ ሲሆን፤ በ2017 ዓ.ም በታህሳስ ወር ወደ 17 በመቶ ዝቅ ብሏል፡፡

👉 የምግብ ዋጋ ግሽበት በ2016 ዓ.ም በታህሳስ ወር 18 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ ብሎ ተመዝግቧል፡፡ ምግብ ነክ ያልሆነው የዋጋ ግሽበት 2016 ዓ.ም ታህሳስ ወር 26 ነጥብ 1 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2017 ዓ.ም በታህሳስ ወር ወደ

👉 14 ነጥብ 4 በመቶ ዝቅ ብሎ እንደተመዘገበ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡ ነገር ግን፤ በአሁን ወቅት የመንግስት ሰራተኛውን ጨምሮ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የኑሮ ውድነትን እየተጎዱ ባሉበት ወቅት እንዴት የዋጋ ንረት ቀንሷል ሊባል ቻለ?

👉 ኢትዮጵያ ከቡና ምርት ከአፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን አረቢካቡና ለአለም በማቅረብ አምስተኛ መሆኗ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ አሁንም በያዝነው ወር በቡና የውጭ ንግድ በአማካይ የ ሶስትነጥብ አምስት ጭማሪ ታይቷል፡፡

👉 በየጊዜውና በየወሩ እየጨመረ የመጣውን የነዳጅ ምርት ዋጋ መጨመር መንስኤው ምንድን ነው?

👉 ህገወጥነትን ለመከላከል፣ ነዳጅን ያለእንግልት ለህብረተሰብ ለማድረስ ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት ተዘርግቶ ችግሩን ለመቅረፍ መንግስት ምን እየሰራ ይገኛል?

👉 በህዝቡ ዘንድ እየተነሱ ያሉ የፍትህ ተደራሽነት ችግር ፣የመልካም አስተዳደርና ብልሹ አሰራሮች ለማረም መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ምን እየተሰራ ነው፣

👉 በበርካታ የሀገሪቱ አካባቢዎች በታጣቂ ሀይሎች በጽንፈኞች ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ይገደላሉ፣ የሰላም እጦት ችግር በዘላቂነት ለመፍጣት ምን እየተሰራ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *