




የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-
የአፈር ማዳበሪያ ስርጭት ላይ መዘግየት እንዳይፈጠር ምን እየተሠራ ነው?
ወደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ የሚወስደው መንገድ በፀጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጧል፤ ይህን ለማስቀጠል ምን እየተሠራ ነው?
የስራ እድል ፈጠራ ለሴቶች እና ለክልሎች ያለው አካታችነት ቢብራራልን፤
ዘላቂ ሰላም ለመገንባት የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር እና ሰላም የማስከበር እርምጃን ለማጣጣም ምን እየተሠራ ነው?
በቤንሻንጉል ለኑሮ ውድነት ማካካሻ ጭማሪ ቢደረግም፤ የመምህራን ያልተከፈለ ውዝፍ ደሞዝ መኖሩ እንዴት ይታያል?
በመተከል ስር የሰደደው የኮንትሮባድ አሰራር እንዲፈታ ምን ታስቧል?
ተጀምረው የተጓተቱ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን ለማፋጠን ምን ዕቅድ ተይዟል?
ወደ ትምህርት ገበታቸው ያልተመለሱ ተማሪዎች መኖራቸውን መረጃዎች ያሳያሉ፤ ይህን ለመፍታት ምን እየተሠራ ነው?
ወረርሽኞችን ቀድሞ ከመከላከል የተወሰዱ እርምጃዎች ምንድን ናቸው? የመድኃኒት አቅርቦትን ለማሻሻልስ ምን እየተሠራ ይገኛል?
