የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ለማድረግ በለውጥ ሂደት ውስጥ አብሮ የሚዘምን የማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ባህል ይዘን መጓዝ ያስፈልጋል ፦ አቶ አልማው ዘውዴ

Spread the love

“ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ቃል ለዞን ፣ ወረዳና ከተማ አስተዳደር አጠቃላይ አመራር የምክክር መድረክ በሚዛን አማን እየተካሄደ ይገኛል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ በምክክር መድረኩ እንደተናገሩት ለውጥ ተፈጥሯዊና የማይቀር ሂደት መሆኑን ገልጸው ከለውጡ ባህል ጋር አብሮ መዘመን እና ራስን ማዘጋጀት ያስፈልጋል።

መደመር ትላንት ፣ ዛሬና ነገን አስታርቆ የሚጓዝ አስተሳሰብ መሆኑን ገልጸው መደመር የኢትዮጵያን ህልም በእውን እያረጋገጠ ነው ብለዋል። እንደ ሀገር የማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ባህልን ማዘመንና ስብራቶችን በመጠገን ወደ አዲስ ባህልና ሁለንተናዊ ብልጽግና ማሻገር ነው ብለዋል።

ብልጽግና ሰብአዊ ልዕልናን ማረጋጥ ፣ ኢኮኖሚያዊ ሉአላዊነትና አፍሪካዊት ሀያል ሀገር መገንባትን ቁልፍ ተግባር አድርጎ እየሰራበት ይገኛል ብለዋል። አለም ቀጣይነት ባለው የለውጥ ሂደት ናት ያሉት ኃላፊው ሀገራችንም አዲስ የፖለቲካ ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ልምምድና ትግበራ ውስጥ ትገኛለች ብለዋል።

ለውጡ ስኬታማ መሆን የሚችለውም ሀሳብን ወደ ተግባር መቀየር የሚችል የአስተሳሰብና የአመለካከት ለውጥ ሲኖር ነው ብለዋል። ገዥ ትርክትን ለማፅናት ሀገራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የገለጹት አቶ አልማው ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል።

መድረኩ ቀጥሎ እየተካሄደ ሲሆን አቶ አልማው ዘውዴ ለምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች ለውይይት መነሻ ሰነድ እያቀረቡ ይገኛሉ።

መረጃው የቤንች ሸኮ ዞን የመንግሰት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *