የጠራ አመለካከትና አስተሳሰብ ያለውን አመራር መገንባት የብልፅግና ፓርቲ ዋነኛ ግብ ነው፦አቶ በላይ ተሠማ

Spread the love

“ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ቃል ለዞን ፣ ለወረዳና ከተማ አስተዳደር አጠቃላይ አመራር የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በሸካ ዞን ማሻ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

የምክክር መድረኩን እየመሩ የሚገኙት የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ በላይ ተሠማ እንደተናገሩት የጠራ አመለካከትና አስተሳሰብ ያለውን አመራር መገንባት የብልፅግና ፓርቲ ዋነኛ ግብ ነው ብለዋል።

ለውጥ ተፈጥሯዊና የማይቀር ሂዴት በመሆኑ ለውጡን ማስቀጠል ደግሞ ከፓርቲው አመራርና አባል ይጠበቃል ሲሉ ገልፀዋል አቶ በላይ።

የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት በብልፅግና ፓርቲ ሸካ ዞን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የዞኑ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ አለሙ እንደገለፁት ሁለንተናዊ ብልጽግናን እውን ለማድረግና ለውጡን ለማስቀጠል አመራሩ ትጉህና ጠንካራ የስራ ባህል ባለቤት መሆን ይጠበቅበታል ብለዋል።

ለቀጣይ የፓርቲው ተልዕኮ አመራሩ ራሱን ማዘጋጀት ይጠበቅበታል ሲሉም ገልፀዋል አቶ አለማየሁ።

በብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ የተዘጋጀውን ሠነድ አቶ በላይ ተሠማ እያቀረቡ ይገኛሉ።

መድረኩን በብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የክልሉ መንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ በላይ ተሠማ፣የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ እና በብልፅግና ፓርቲ የሸካ ዞን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ አለሙ በጋራ በመሆን እየመሩ የሚገኙ የዞን ማዕከልን ጨምሮ የሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር አጠቃላይ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

መረጃው የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *