

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 1ኛ መደበኛ ስብሰባው ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ መስከረም 26/2018 ዓ.ም ለሁለቱ ምክር ቤቶች ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበን የድጋፍ ሞሽን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
በ6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባው በሁለት አጀንዳዎች ላይ ውይይት አካሂዷል።
በዚህም ምክር ቤቱ በመጀመሪያ አጀንዳም በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ-ጉባኤን መርምሮ በማጽደቅ ስብሰባውን ጀምሯል።
በመቀጠልም በ1ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ መስከረም 26/2018 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መደበኛ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበን የድጋፍ ሞሽን አዳምጧል።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጂጌ(ዶ/ር) የድጋፍ ሞሽኑን አቅርበዋል።
በመጨረሻም የምክር ቤቱ አባላት ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ መስከረም 26/2018 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መደበኛ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበውን የድጋፍ ሞሽን ካዳመጡ በኋላ በሙሉ ድምጽ አጽድቀውታል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
