የብልጽግና ፓርቲ ሴቶችን በማህበራዊ ፣ በፖለቲካ ፣ በኢኮኖሚ እንዲሁም በሁሉም ዘርፍ ሁለንተናዊ ተሳታፊና ተጠቃሚ በማድረግ ታላቅ ሃገር የመገንባት ራዕይ ይዞ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ

Spread the love

በንቅናቄ መድረክ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የገበያ ልማት ዘርፍ ኃላፊ ፓርቲያችንን እንደ ሀገር በተለይ እየተካሄደ ባለው በሃገረ መንግስት ግንባታ ሴቶች ሚና እጅግ በጣም የጎላ በመሆኑ ሴቶችን በማህበራዊ ፣ በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ በሁሉም ዘርፍ ሁለንተናዊ ተሳታፊና ተጠቃሚ በማድረግ ትልቅ ሃገር የመገንባት ራዕይ ይዞ እየሰራና በተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው ብለዋል።

አያይዘውም የብሔራዊነት ገዥ ትርክትን ከማጽናት ጋር ተያይዞ ሴቶች ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን ውስጥ፣ በፖለቲካ ውሳኔ ሰጪነት ፣በህዝብ ምክር ቤቶች ፣ በአስፈጻሚ አካላት ብሎም በህጋዊ መዋቅር በሁሉም ደረጃ መስራት ይችላሉ ውጤት ማምጣት ይችላሉ የሚለውን በተገቢው ሴቶችን ውጤታማ ጭምር አድርጎ እየሰራ እንደሆነ ወ/ሮ አሰገደች ተናግረዋል።

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አሰገደች ፍቅሩ እንደተናገሩት ሴቶች በሀገር ግንባታ ውስጥ ከፍተኛ ሚና ያላቸው ሀገር መገንባት የሚችሉ መሰረት እንደሆንን ይታመናል በማለት ሴቶች በተለያየ ምክንያት ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጉዞ ውስጥ ወደኋላ የሚጎትታቸው ነገሮች ስላሉ እንዲህ አይነት መድረኮችን በመሳተፍ ፓርቲው እና መንግስት የሚያስቀምጣቸውን አቅጣጫ በመቀበል የሀገር ግንባታው ላይ ከፍተኛ የሆነ አስተዋጽኦ ማበርከት ያስፈልጋል ብለዋል።

በመድረኩ ጥያቄና መልስ ውድድር እንዲሁም የተለያዩ ዝግጅቶ ተካሂዳል።

ከክልል፣ከዞን፣ከከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የብልጽግና ፓርቲ ህብረት አመራሮችና አባላት በመድረኩ ተሳትፈዋል ሲል የዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *