ቢስት ባርን ለማክበር የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል

Spread the love

የበዓሉን ዝግጅት አስመልክቶ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን መግለጫ ሰጥተዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አቶ ሃብታሙ ካፍትን በሰጡት መግለጫ የ”ቢስት ባር” ጥር 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም በዓሉ በተለያዩ ክዋኔዎች በድምቀት ይከበራል ብለዋል።

የቢስት ባር አዲስ እህል መግባቱን ተከትሎ የሚከበር በዓል ስሆን በቤንች ብሔር ዘንድ ለፈጣሪ ምስጋና የምቀርብበት ነው ብለዋል።

በዓሉ የመጀመሪያ ወይም የበኩር በዓል የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን በክረምት የተዘራ አዝመራ ደርሶ የመጀመሪያው እህል ደርሶ በጋራ በሚቀመስበት ወቅት የሚከበር በዓል እንደሆነም ገልጸዋል።

የቢስት ባር በዓሉ የእርቅ፣ የሰላም፣ ይቅርታና የወንድማማችነት እና እህትማማችነት የሚንጸባረቅበት እንጂ ከሃይማኖታዊ ስራርዓትና ባዕድ አምልኮ ጋር ፈጽሞ የሚገናኝ አይደለም ብለዋል።

በተጨማሪም በዓሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው እጅግ የጎላ እንደሆነ አመልክተዋል።

በዓሉን ዘንድሮ እሴቱን በጠበቀ መልኩ ለማከበር የሚያስችል ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውንም አስተዳዳሪው ገልጸዋል።

በዓሉ በዞኑ የሼይ ቤንች ወረዳ “ዣዥ” ቀበሌ እንዲሁም በሚዛን አማን ከተማ የተላያዩ እንግዶች በተገኙበት በልዩልዩ ዝግጅቶች በድምቀት እንደሚከበርም ገልጸዋል።

አቶ ሀብታሙ ካፍትን እንኳን ለቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ “ቢስት ባር” በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል ሲል የቤንች ሸኮ ቴቪ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *