የምክክር ኮሚሽኑ የስራ ዘመን ተራዘመ

Spread the love

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሶስት ዓመታት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በመመርመር ለኮሚሽኑ የ1 ዓመት ተጨማሪ የስራ ዘመንን ሰጥቷል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ጉዳዮች ኮሚቴ የኮሚሽኑን የስራ ሂደት ከገመገመ በኋላ ባደረገው ምልከታ ኮሚሸኑ አጠቃላይ ስራውን ማጠናቀቅ እንዲያስችለው የስራ ዘመኑ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ምክረ ሃሳብ አቅርቦ ነበር፡፡

ምክር ቤቱ ኮሚሽኑ ዋና ዋና እና አንኳር ቀሪ ስራዎች መኖራቸውን በማመን የስራ ዘመኑ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም በ3 ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

አባላቱ ኮሚሽኑ በተሰጠው ተጨማሪ የስራ ዘመን ተጠባቂ ቀሪ ስራዎችን እንዲያጠናቅቅ ጠይቀዋል።

የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የኮሚሽኑ የስራ ዘመን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማራዘም እንደሚቻል ይደነግጋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *