



ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑ አስፈጻሚ አካላትን የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት አፈጻጸም፣ ዛሬ ገምግመናል፡፡
ባለፉት ስድስት ዓመታት መንግሥታችን ለጠንካራ ተቋማት ግንባታ በልዩ ትኩረት ሠርቷል። በተለይም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት ራሳቸውን በአግባቡ በማደራጀት ለሀገር ግንባታ የሚቆጠር አስተዋፅዖ በማበርከት ላይ ናቸው።
በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ መስኮች ባለፉት ስድስት ወራት የተመዘገቡ ስኬቶች የተቋሞቻችን የመፈጸም አቅም ማሳያ ናቸው።
በቀጣይም ተቋማቱ የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ ለማሳካት አገልግሎት አሰጣጣችንን ማዘመን፣ ወጪ ቆጣቢ አሰራርን መከተል፣ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እና በተሰጠን ተልዕኮ የምንፈጥረውን በጎ ተፅዕኖ እንዲሁም የተገኙ ውጤቶችን በቀጣይነት እየገመገሙ መሄድ አስፈላጊ መሆኑን አቅጣጫ አስቀምጠናል፡፡
