





የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው አፈ-ጉባኤዎች የጋራ ፎረም መድረክ ላይ እየተሳፈ የሚገኘው የተለያዩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች በክልሉ በቤንች ሸኮ ዞን የልማት ስራዎችን ጉብኝት እያደረገ ይገኛል፡፡
ከትላንትና ጀምሮ በክልሉ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ምልከታ ማድረግ የጀመረው የክልልና ከተማ አስተዳደር የአፈጉባኤዎች ቡድን በዛሬ በቤንች ሸኮ ዞን እየተሰራ ያለውን የጠቅላይ ሚንስትሪ ዶክተር አብይ አህመድ ኢንሼቲቪ የሆነው የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት የደንቢ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ሎጅና የሚዛን አማን ኤርፖርት ግንባታ ጉብኝት እያደረገ አድርገዋል፡፡
የደንቢ ሰው ሰራሽ ሀይቅና ከዚህ ቀደም ሲል ለበበቃ ቡና ልማት እና ለሚዛን አማን ከተማ ነዋሪዎች ለ10 ዓመታት የመብራት አገልግሎት ይሰጥ እንደነበረ እና አሁን የገበታ ለትውልድ አንዱ አካል ሆኖ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ መሆኑንና በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀመርም ተገልጿል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አፈጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፤ ክልሉ ለሀገር የሚበቃ የተፈጥሮ ሀብት እንዳለውና በክልሉ የቤንች ሸኮ ዞን ተፈጥሮ በራሱ የለገሰው አካባቢ መሆኑን ጭምር በጉብኝቱ መመልከት መቻላቸውን ጠቁመዋል፡፡
የሚዛን አማን ከተማ ትልቅ የንግድና ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ያለበት ከመሆኑም ባሻገር ትላልቅና ግዙፍ የተለያዩ የልማት ስራዎች እያየን ነው ብለዋል፡፡
አይናችን በመግለጥ ያሉንን ጸጋዎች በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል ያሉት ወ/ሮ ፋጤ፤ የደንቢ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ሎጅ ማህበረሰቡን የሚያዝናና ለኢትዮጵያ የሚተርፍ ትልቅ የቱሪዝም መዳረሻ ሎጅ እንደሆነ አንስተዋል፡፡
ማህበረሰቡና አመራሩ ይህንን በየአካባቢው ያለውን ጸጋ አውጥቶ ለመጠቀም በደንብ መስረት እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
የቤንሻንጉል ክልል አፈጉባዔ ወ/ሮ አስካለ አልቦሮ ፤ የብልጽግና ጉዞአችንን እውን ለማድረግ ሁለንተናዊ በልጽግና በማረጋገጥ የአካባቢያችን ተፈጥሮ ሀብት በተለያየ መንገድ ለመጠቀም ማልማትና ለትውልድ ማስተላላፊ ይጠበቃል ነው ያሉት፡፡
ለዚህም ከትናንት ጀምሮ በክልሉ እያየን ያለው ነገር በጣም የሚደነቅ ነው ብለው በእርግጥም ሁለንተናዊ በልጽግና በማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉት ጅምር ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆኑንና ይህንን ለማስቀጠል የሁሉም ኃላፊነት ያለበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ወደክልላቸው በሚመለሱበት ወቅት ሌሎች አካባቢዎች ያልታዩ የተፈጥሮ ጸጋዎችን በተገቢው መንገድ ተጠቅሞ የማልማት እና አሻራን ለቀጣይ ትውልድ ማስተላላፊ የሚጠናከርበትን እና ልምድ የሚወሰድበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የአፈጉባኤዎች ፎረሙ የበቃ ቡና ልማት ፕሮጀክት እና በክልሉ ምክር ቤት የተዘጋጀ የክልሉን ገጽታ የሚገልፅ ዶክመንተሪ ቀርቦ ምክክር የሚደረግና ማጠቃለያ ተደርጎ ፎረሙ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡
በክልሉ እየተደረገ ያለው የአፈጉባኤዎች የጋራ ፎረም ዋና ዓላማ የልምድ ልውውጥ ማድረግና መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች ላይ ለመምከር ያለመ ስሆን፥ ከዚህ በተጨማሪ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን የሚያጠናክር ነው፡፡
በተከተል ወ/ሚካኤል
