




“በመደመር መንግሥት እይታ፤የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሃሳብ ሲሰጥ የቆየው የካፋ ዞን 3ኛ ዙር አመራሮች ስልጠና በስኬት ተጠናቋል ።
የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ አጠቃላይ የሥልጠና ቆይታ አስመልክቶ ማጠቃለያና ቀጣይ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል::
አመራሩ የተያዙ የብልጽግና ግቦችን ለማሳካት በጠንካራ የአመራር ቁርጠኝነት፣ ፈጠራ፣ ፍጥነትና ዝላይ መርሆዎችን ተከትሎ በመስራት ፈጣን ለውጥ ማስመዝገብ ይጠበቅበታል ብለዋል ።
ከስልጠና በኋላ አመራሩ ቅንጅታዊ አስራርን ማጠናከር ፣ የአመለካከት እና የተግባር ለውጥ ማምጣት ፣ የእይታ ለውጥ ማሳደግ እና በትንሽ ውጤት መርካትን በመተው ትላልቅ አገራዊ ግቦችን አቅዶ መስራት አለበትም በማለት አሳስበዋል።
አመራሩ ከጠባቂነት ስሜት በመላቀቅ በየደረጃው የሚነሱ የህዝብ የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን ፈጣን ምላሽ መስጠት እንዳለበት አቶ እንዳሻው ከበደ ገልጸዋል ።
በየደረጃ ያለው አመራር ብልጽግና ፓርቲ እና የለውጡ መንግስት ቀጣይ ለመስራት ያስቀመጣቸውን ስትራቴጂካዊ ግቦችን አውቆ በጥራትና በፍጥነት መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል።
በሀገራችን የተያዘውን አምስት የዕድገት ተኮር ዘርፎች ላይ በቂ እውቀት ፣ግንዛቤና ክህሎት አግኝተው ወደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ በመቀየር አመራሩ መስራት እንዳለበት ዋና አስተዳዳሪው አስገንዝበዋል ።
በአጠቃላይ የቦንጋ ከተማ የዕድገት ጉዞና የመልሶ ማልማት ሥራ እንቅስቃሴን በየደረጃው ያለው አመራር መደገፍ እንዳለበት አቶ እንዳሻው አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል ሲል የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
