ከ27 ሺ በላይ ዲጂታል መፅሃፍቶች የተጫነው የዶ/ር ጉነት ጥላሁን ዲጂታል ላይብረሪ በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ በይፋ ተመርቋል።

Spread the love

በአቶ ለማ እና ዶ/ር ጉነት ጥላሁን ፋውንዴሽን ሙሉ ወጪ የተደራጀው የዳውሮ ዞን ሂዶታ ትምህርት ቤት የዲጂታል ላይብረሪ በይፋ ተመርቋል።

ላይብረሪው 51 ኮሚፒዩተሮችን፣ የኢንተርኔት አገለግሎትንና 27 ሺ ዲጂታል መፅሀፍቶችን የያካተተ ነው።

ላይብረሪው በዞኑ የማጣቀሻ መፅሀፍት እጥረት ችግር በመቅረፍ የተማሪዎችን መጠነ ማለፍ እንደሚጨምር የተጠቀሱት በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢንዱስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና የማረቃ ገና ምርጫ ክልል ተወካይ ዶ/ር አማረች በካሎ ናቸው።

ዶ/ር አማረች በካሎ ፋውንዴሽኑ ላይብረሪውን እንዲከፍት ከፋውንደሽኑ ባለቤቶች ጋር በመገናኘትና ጥያቄ በማቅረብ ስላደረጉት ሰፊ ጥረት ምስጋና ቀርቦላቸዋል።

የልማት ማህበሩ በመንግስት ያልተሸፈኑ የልማት ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል ያሉት የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ ሂዶታ ትምህርት ቤት ከ2014 ጀምሮ ላለፉት አራት አመታት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልቀቂያ ፈተና ያስፈተናቸውን ተማሪዎች በሙሉ ማሳለፍ ችሏል ብለዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊና የስርዓተ ትምህርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አባተ ኡቃ በበኩላቸው በክልሉ ባለፉት ተከታታይ አመታት የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል በተሰራው ስራ ለውጥ እየመጣ ያለ ቢሆንም በሚፈለገው ልክ ውጤት ለማስመዝገብ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስአድተዋል።

በምረቃው የተገኙ የአቶ ለማ እና ዶ/ር ጉነት ጥላሁን ፋውንዴሽን ስራ አስኪያጆ ዶ/ር ዳንኤል ድጋፌ ፋውንዴሽኑ በትምህርት፣ በንፁህ መጠጥ ውሃና በሌሎች ዘርፎች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል ሲል የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ መረጃ ያመላክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *