በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እየተከናወኑ ያሉ የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አፈጉባኤዎች ተናገሩ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው የጋራ ፎረም እየተሳተፉ የሚገኙ የክልሎች እና ከተማ አስተዳደር አፈጉባኤዎች በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እየተከናወኑ ያሉ የግብርናና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባእንደሚገባ ተናግረዋል።

የፎረሙ ተሳታፊ አፈጉባኤዎች በቦንጋ ዩኒቨርስቲ የሙዝ ልማት፣ የሌማት ትሩፋት አንዱ አካል የሆነውን የከብቶች እርባታ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ስራዎች እና በመማር ማስተማሩ ዘርፍ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች ተዛውረው ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ አጠቃላይ ገለጻ ያደረጉት የዩኒቨርስቲው ምክትል ፕረዚዳንት ዶክተር ከላለው አዲሱ፤ ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን አካባቢውን ጸጋ መነሻ በማድረግ በግብርና እና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ላይ ትኩረት አድእየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ዘርፍ ዩኒቨርሲቲው ሰፋ አድርጎ በመስራት ወደ ፊት የልህዕቀት ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ያለ ስራ መኖሩን ለወደፊቱም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንዳለም ጠቁመዋል፡፡

የጉብኝቱ ተሳታፊዎች የክልልና ከተማ አስተዳደር አፈጉባኤዎች፤ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በመማር ማስተማር፣ በማህበረሰብ አገለግሎት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ጠበቃው ዘርፍ እያከናወነ ያለው ዘርፈ ብዙ ስራዎች ሌሎች ዩኒቨርስቲዎችም ጭምር ምርጥ ተሞክሮ የሚሆን መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እንደክልል የቱሪዝም ጸጋ ወደ ሀብት በመቀየር ከዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ ዩኒቨርሲቲዎች ትልቅ ሚና ያላቸው በመሆኑ በዚሁ ዘርፍ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚጠበቅ ጠይቀዋል፡፡

በክልሉ 13 ነበር ብሔረሰቦችና ሌሎች በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች መኖሪያ ከመሆኑ አንፃር የብሔሰቦችን ቱባ ባህል፣ ቋንቋና ትሁፍት በምርምርና በጥናት በማስደገፍ ለማሳደግ ተጠቀሚነቱን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይገባልም ብለዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ውስጥ እየተሰሩ ያሉ አጠቃላይ ተግባራት ከክልሉ አልፎ ለሀገሪቱ ትልቅ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንስተው ይህንን ሁሉ አቀፍ ተግባራት መንግሥት መደገፍና የበለጠ ማጠንከር እንደሚጠበቅም ገልጸዋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ በበኩላቸው፤ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲው እየሰራ ያለው ሞዴል ስራዎች በተለይም የግብርና ልማት ስራዎች ማስፋት እንዳለበት ገልፀው ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር በኩል የተለያዩ ዲፓርትሜንቶችን በማስፈትና ተማሪዎችን ተቀብሎ ከማስተር አኳያ ያለውን ተግባር ማጠንከር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ቡና ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ እየሰጣያለው ጠቀሜታው እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ለዚህም የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የቡና ድፓርትመን ከፍቶ የመማር ማስተማር ስራ እያከናወነ መሆኑ የሚመሰገን እንደሆ ጠቅሰው በተለይም በቡና ድፓርትሜን የተማሪዎችን የቅበላ መጠን በማሳደግ የቡናው ዘርፍ ላማሻገር ትኩረት ተሰጥቶ መስራት እንደሚጠይቅም ገልፀዋል፡፡

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *