በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር ከበጋ መስኖ ስንዴ የተሻለ ምርት እንደሚጠብቁ አርሶ አደሮች ገለፁ

Spread the love

የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከተረጅነት ወደ ምርታማነት መስፈንጠሪያ መሆኑን የወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ገለጸ፡፡

አርሶ አደር አበሻ ዳሮታ እና ደባልቄ ዳራ በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር የጨታ ቀበሌ ነዋሪዎች ሲሆኑ የበጋ መስኖ ስንዴ እያለሙ ከሚገኙ አርሶ አደሮች መካከል ናቸው።

አርሶአደሮቹ የማሳ አረም ስራ ላይ ተሰማርተው ያገኘናቸው ሲሆን በሰጡትም አስተያየት ከባለፈው አመት ጥሩ ተሞክሮ በመውሰድ የዘንድሮውን የበጋ መስኖ ስንዴ በተመሳሳይ ወደ ማምረት መግባታቸውን ነው የገለጹት።

የዘንድሮ የአየር ፀባይ ምቹ መሆኑን አክለው የተናገሩት አርሶአደሮቹ፥ ከግብርና የሰብል ባለሙያ በተሰጣቸው ሙያዊ ድጋፍ በመታገዝ የወቅቱን እርሻ አስፈላጊውን ግብአት ተጠቅመው የዘሩ መሆናቸውንና ከዚህም የተሻለ ምርት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።

አርሶ አደሮቹ አያይዘውም ከአንድ ሄክታር ከ45 እስከ 50 ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅና አሁን ላይ 10 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈናቸውን ገልፀዋል።

በከተማ አስተዳደሩ የጨታ ቀበሌ የሰብል ባለሙያና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ ጌታሁን ጊቲማ አርሶ አደሮቹ ከመጀመሪያው ምዕራፍ ጀምሮ በቂ ሙያዊ ድጋፍ ሲሰጣቸው እንደነበር ገልጸው፥ ቴክኖሎጂን በአግባቡ በመጠቀምና የተሰጣቸውን ሙያዊ እገዛ ተግባራዊ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስረድተዋል።

ከወቅቱ እርሻ አመርቂ ውጤት እንደሚገኝ ሙሉ ተስፋ መሰነቃቸውንም ተናግረዋል።

በኮንታ ዞን የአመያ ከተማ አስተዳደር የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ ወዳጀ በ በ2018 የበጋ መስኖ ስንዴ 50 ሄክታር መሬት እንደ ከተማ አስተዳደር በበጋ ስንዴ ለመሸፈን መታቀዱን ገልጸዋል።

አብዛኛው በኩታ ገጠም እርሻ የሚሸፈን ነው ያሉት ሃላፊው በዚህም በከተማ አስተዳደሩ በጨታ ቀበሌ 10 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ በስንዴ መሸፈኑን ገልፀዋል።

በወረዳው ከበጋ መስኖ ስንደ ከ500 በላይ ኩንታል ምርት ለማግኘት ግብ ተጥለው እየተሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል ሲል ደሬቴድ ዘግቧል።

የተቀናጀ የበጋ መስኖ ስራ የዕቅድ በሁሉም ዘርፎች የተሻለ ውጤት ለማምጣት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *