




ከክልሉ ወረዳዎች ለተውጣጡ የኦዲት እና ኢንስፔክሽን ባለሙያዎች ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቋል።
የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ እንደተናገሩት፣ስልጠናው የውስጥ ኦዲት እና ኢንስፔክሽን ላይ ያለውን ግንዛቤ በማሳደግ የፋይናንስ ዘርፍ አሰራር ስርዓቱን ለማሳደግ ያለመ ነው ብለዋል።
በክልሉ ለሚገኙ የውስጥ ኦዲት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች አቅም በመፍጠር ክትትልና ድጋፍ በማድረግና በማስተባበር ያለውን ውስን ሀብት በአግባቡ ስራ ላይ እንዲውል ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራም ገልጸዋል።
የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ምክትል እና የፊስካል ፖሊሲ እና መንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ መለሠ ኡሮ እንደተናገሩት፣የኦዲት ባለሙያው በፋይናንሻልና በገቢ ግብር መመሪያ ላይ በቂ እውቀት አግንኝቶ የኦዲት ስራውን በተደራጀና ተጠያቂነት ባለው መልኩ መፈጸም እንዳለበት ተናግረዋል።
በቢሮው የትሬዤሪና የመንግስት ሂሳብ ማጠቃለያ ዳይሬክተር አቶ አበባዬሁ ኡቶ በበኩላቸው፣የገቢ ግብር ኦዲት ጨምሮ በመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር፣ በክፍያና የሂሳብ አያያዝ፣ በመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር የፋይናንሻል ኦዲት አደራረግ እና በመንግስት ፋይናንስ የሂሳብ አሰራር ላይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንዲቻል በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አስረድተዋል።
በካሳሁን አሰፋ
