በሚቀጥሉት ቀናቶች አንጻራዊ የደመና ሽፋን መጨመር ይኖራል

Spread the love

በሚቀጥሉት ቀናቶች በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ አንጻራዊ የእርጥበት መጠንና የደመና ሽፋን መጨመር እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

በሚቀጥሉት ቀናቶች ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በጥቂት የመካለኛው፣ በምሥራቅ፣ በሰሜን ምሥራቅ፤ በሰሜን ምዕራብ እንዲሁም በደቡብ ኢትዮጵያ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ አንጻራዊ የእርጥበት መጠንና የደመና ሽፋን መጨመር እንደሚኖር የትንበያ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም የደቡብ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ምዕራብ እና የምዕራብ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንሚያገኙም ነው የኢንስቲትዩቱ መረጃ የሚያመላክተው፡፡

በሌላ በኩል አሁን ላይ እየተስተዋለ ያለው የበጋው ደረቅ፣ ጸሀያማ እና ነፋሻማው የአየር ሁኔታ በሚቀጥሉት ቀናትም ቀጣይነት እንደሚኖረው አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ተብሏል ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *