በክልሉ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና በዘርፋ የስራ ዕድል ፈጠራን ለማጠናከር በእንሰሳት ሀብት ልማት ስራ ላይ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ።

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ ለዞንና ወረዳ የእንስሳት ዘርፍ ሃላፊዎች እና ጤና ባለሙያዎች ክልላዊ የእንስሳት ጤና ኤክስቴንሽን ማስጀመሪያ እና የእንስሳት ጤና ፓኬጅ ስልጠና መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ የእንስሳት ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ እንሰሳት ጤና ዳይሬክቶሬት ከምግብ ሥርዓት ማጣናከሪያ ኘሮግራም ጋር በመተባበር በተዘጋጀው መድረክ ላይ በቢሮው የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ታመነ በቀለ ባደረጉት ንግግር፣በክልሉ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና በዘርፋ የስራ ዕድል ፈጠራን ለማጠናከር በእንሰሳት ሀብት ልማት ስራ ላይ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በክልሉ የተጀመረው የሌማት ትሩፋት ኢንሼትቨ ከተጀመረ ወዲህ የእንሰሳት ሀብት ልማት ዘርፍ ተሳትፎ በከፍተኛ ሁኔታ መነቃቃት ማሳየቱን ተናግረዋል።

ስለሆነም በእንሰሳት ሀብት ልማት ውጤታማ ለመሆን የእንስሳት ጤናን መጠበቅ፣የእርባታ ጣቢያዎችን ማዘመን እና በሚገባ መከታተል አስፈላጊ በመሆኑ የእንስሳት ጤና ኤክስቴንሽን ራሱን ችሎ እንዲደራጅ መደረጉን ገልፀዋል።

በቢሮው የእንስሳት ጤና ዳይሬክተር ዶክተር ብርሃኑ አለማየሁ፣በእንስሳት ጤና ኤክስቴንሽን ሚና ላይ ስልጠና በሰጡበት ወቅት እንዳብራሩት፣እያደገ የመጣውን የእንስሳት ሀብት ልማት ውጤታማነት ለማስቀጠል የሚያስችል አዲስ የእንሰሳት ጤና ኤክስቴንሽን መሪ ዕቅድ መዘጋጀቱን ጠቅሰው ይህንን እስከታችኛው ፈጻሚ አካላት ማውረድ እና ተፈፃሚ ማድረግ እንደሚገባ አስረድተዋል።

በካሳሁን አሰፋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *