



በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቀጠና ግብርናን ለማዘመን ታስቦ በቦንጋ የተገነባው የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና የሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል እ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እና የኢፌዲሪ ግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ግርማ አመኒቴ (ዶ/ር) በተገኙበት ተመርቀው ተከፍቷል።
ኮርፖሬሽኑ በቦንጋ ከተማ በ743 ሚሊዮን ብር፣ በ2.5 ሄክታር መሬት ላይ ያስገነባው ማዕከሉ በውስጡ ባለ አራት ወለል የአስተዳደር ህንጻ፣ በአመት ከ150ሺህ ኩንታል በላይ ዘር ማዘጋጀት የሚያስችል ዘመናዊ የዘር ማበጠሪያ ማሽን፣ የግብርና ግብዓት ማከማቻ መጋዘኖች፣ የእርሻ መሳሪያዎችና ቴክኖሎጂ ማሳያ እንዲሁም ዘመናዊ የዘር ቁጥጥር ላብራቶሪን ያካተተ መሆኑን መሆኑ ተመላክቷል።
ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት ከፍት የኾነው ማዕከሉ በዋናነት ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ ከፊል ኦሮሚያና ጋምቤላ ክልሎች ተደራሽ በመሆን የተሟላ የዘርና ግብርና ግብዓት አቅርቦት፤ የአፈር ማዳበሪያና ፀረ ተባይ ኬሚካል አቅርቦት፤ የእንሳሳት መድኃኒት አቅርቦት፣ የተፈጥሮና ኬሚካል ማዳበሪያ እንዲሁም የእርሻ የሜካናይዜሽን አገልግሎት የሚሰጥ ነው።
በምረቃው ስነ ስርዓት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ-አፈጻሚ አቶ ክፍሌ ወ/ማርያምን ጨምረው ሌሎች የፌዴራል እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የአከባቢው የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
በዕድገቱ በዛብህ
