ቢስት ባር ዕሴት የወል እውነትና የኅብረ ብሄራዊነት መሠረት ነው – የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር

Spread the love

ቢስት ባር ዕሴት የወል እውነትና የኅብረ ብሄራዊነት መሠረት ነው – የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር

የቤንች ብሄር የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል የኾነው ቢስት ባር በሚዛን አማን ከተማ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢፌዲሪ ፌደሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር፥ የቢስት ባር ዕሴት የወል እውነትና የኅብረ ብሄራዊነት መሠረት ነው ብለዋል።

ቢስት ባር ከተፈጥሮና ከግብርና ሥራዎች ጋር የሚገናኝ በመኾኑ ይህንን መልካም ዕሴት በማጠናከር የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በዓሉ ኢትዮጵያዊያንን በአንድነት በማሰባሰብ የህዝቦች አንድነትን የሚያጠናክር፣ እርቅና ይቅርታ የሚደረግበት ታላቅ የማኅበረሰብ መገለጫ የኾነ በዓል እንደኾነም አቶ አገኘሁ ተናግረዋል።

የቢስት ባር ባህል ዕሴቱን ሳይለቅ ለትውልድ እንዲተላለፍ የታሪክ ምሁራን በቅንጅት እንዲሰሩም አቶ አገኘሁ አሳስበዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌በሊንክደን

https://www.linkedin.com/company/southwest-communications

📌በትሬድስ

https://www.threads.com/@southwest_communications

📌በብሉ ስካይ

https://bsky.app/profile/swc79.bsky.so

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *