የቢስት ባር ዕሴት በማጎላት ለክልላዊ አንድነት መጠናከር መጠቀም ይገባል – ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

Spread the love

የቢስት ባር ዕሴት በማጎላት ለክልላዊ አንድነት መጠናከር መጠቀም ይገባል – ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

የቤንች ብሄር የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል የኾነው ቢስት ባር በሚዛን አማን ከተማ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

የቢስት ባር ዕሴት የኾኑ ሠላም፣ልማትና አብሮት በማጉላት ለክልላዊ አንድነት መጠናከር መጠቀም እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የብዝሀ ማንነት ባለቤት የኾነች ጥንታዊት ሀገር ናት ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ከእነዚህ ውብ የብዝሀ ማንነቶች መካከል የቤንች ብሄር ባህል አንዱ መኾኑን ጠቁመዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን በክብር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት ተግባራዊ የኾነው የቱሪዝም መዳረሻ ልማትና የአዉሮፕላን ማረፊያ እየተሰራ ያለበት አከባቢ መኾኑን የገለጹት ዶ/ር ነጋሽ፥ የቢስት ባር በዓል የኢኮኖሚ ፋይዳ በማሳደግ ለአከባቢው ተጨማሪ የቱሪዝም ሀብት ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ቢስት ባር የቤንች ብሄር ቱባ ባህልና ታሪክ እንዲሁም ባህላዊ ክዋኔዎች በአደባባይ የሚያንጸባርቅ በዓል መኾኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በዓሉን ለማኅበረሰብ ሁለንተናዊ ለውጥ መጠቀም እንደሚገባም ተናግረዋል።

የብሄረሰቡ ምሁራን ቱባ ባህሉ መሠረቱን ሳይለቅ ለትውልድ እንዲተላለፍ በጥናትና ምርምር ማዳበር፣ ማልማትና ማስተዋወቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ቢስት ባር ከባህላዊ ኩነት ባሻገር በብሄረሰቡ ዘንድ ዘርፍ ብዙ ትርጉም ያለው ህዝባዊ በዓል መኾኑን የገለጹት የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ከፍተን፣ በዓሉ ህዝቦችን በጋራ በማሰባሰብ ማኅበረሰባዊ መስተጋብር የሚያጠናክር ነው ብለዋል።

ቢስት ባር የክረምቱን ጎርፍና ጭጋግ አልፈን ፣ አዝመራው ለፍሬ በቅቶ ፣ ማሩም ተቆርጦ ለቤት ሲበቃ ለፈጣሪ በጋራ ምስጋና የሚቀርብበት ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የበኩር እሸት ቅምሻ ስነ ስርዓቱና ምርቃቱ ከምድራችን በሽታና ርሀብ እንዲርቅ ፣ ቂምና ቁርሾ እንዲወገድ እንዲሁም አብሮነት ፣ አንድነትና ወንድማማችነት እንዲጠናከርና ሰላም እንዲሰፍን በቤንች ምድር በረከት እንዲሞላ የሚመረቅበት ስርዓት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ቢስት ባር ከቤንች ብሄር ቱባ የባህል ሀብቶች መካከል አንዱ መኾኑን የጠቆሙት አቶ ሀብታሙ፥ በዓሉን ቀጣይነት ባለው መልኩ ማልማትና መጠበቅ ከባለድርሻ አካላት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌በሊንክደን

https://www.linkedin.com/company/southwest-communications

📌በትሬድስ

https://www.threads.com/@southwest_communications

📌በብሉ ስካይ

https://bsky.app/profile/swc79.bsky.so

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *