የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ “ቢስት ባር” በታሪካዊ መነሻው በድምቀት ተከበረ

Spread the love

የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ “ቢስት ባር” በታሪካዊ መነሻው በድምቀት ተከበረ

የቤንች ብሔር የራሱ የዘመን አቆጣጠር ማሳያና አዲስ ዘመን የሆነው “ቢስት ባር” የዘመን መለወጫ በዓል፣ የብሔሩ መነሻና የታሪክ መፍለቂያ በሆነችው በሼይቤንች ወረዳ ዣዥ ቀበሌ በታላቅ ድምቀትና ስነ-ስርዓት ተከብሯል። በዓሉ የብሔሩን ቱባ ባህል፣ አንድነትና ለፈጣሪ ያለውን ምስጋና የሚያንጸባርቅ ነበር።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፀጋዬ ማሞ፣ ኢትዮጵያ የበርካታ ባህሎችና ቅርሶች ባለቤት መሆኗን አስታውሰው፣ መንግስት እነዚህን እሴቶች ለመደገፍና እንዲለሙ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። ቢስት ባርን በመሰሉ በዓላት ውስጥ ያለውን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ በአግባቡ መጠቀም ይገባል ብለዋል።

የቤንች ህዝብ የበኩር እህሉን ቀምሶ ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ሲሸጋገር ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበትና አዲስ ተስፋ የሚሰንቅበት ልዩ ጊዜ መሆኑን የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን ገልጸዋል። አዲስ እህል ሲደርስ ከማህበረሰቡ ጋር በጋራ ተካፍሎ በመቅመስ፣ ከአሮጌው ወደ አዲስ ዓመት የምንሸጋገርበት ውብ ባህላዊ እሴታችን ነው ብለዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን እንደተናገሩት፣ “ቢስት ባር” የቤንች ብሔር የራሱ የሆነ የማንነት መገለጫ፣ ውብ ባህልና ጥልቅ ትውፊት ያለው መሆኑን ያሳያል። በዓሉ ከሩቅም ከቅርብም ያሉ የማህበረሰቡ አባላት የሚሰባሰቡበት፣ ለታላላቆች አክብሮት የሚሰጥበት፣ ለወጣቶች ምክር የሚለገስበትና “የመደመር እሳቤ” በተግባር የሚገለጽበት መሆኑን ጠቁመዋል። “ይህ በዓል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን የሚያጠናክር፣ አንድነትን፣ ሰላምንና ፍቅርን የሚያጸና ትልቅ ፋይዳ አለው” ሲሉ አክለዋል።

በዓሉ የብሔሩ መነሻ በሆነው በታሪካዊው ዣዥ መከበሩ ልዩ ትርጉም እንዳለው ተገልጿል። የሼይቤንች ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ክፍሌ ጎበዜ፣ ታሪካዊ ቦታ የሆነውን ዣዥን ጠብቀው ላቆዩት አባቶች ያላቸውን ምስጋና ገልጸዋል።

በመጨረሻም፣ ይህ ውብ በዓል ያልተበረዘውን የቤንች ባህልና እሴት ጠብቀው ለአዲሱ ትውልድ ላስተላለፉ ቀደምት አባቶች ልዩ ምስጋና የቀረበበትና የብሔሩን ቀጣይነት ያረጋገጠ መሆኑ ተገልጿል ሲል የዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌በሊንክደን

https://www.linkedin.com/company/southwest-communications

📌በትሬድስ

https://www.threads.com/@southwest_communications

📌በብሉ ስካይ

https://bsky.app/profile/swc79.bsky.so

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *