ክልላችን በተጠናከረ የአመራር ቁርጠኝነትና የህብረተሰብ ተሳትፎ አመርቂ ዉጤቶችን እያስመዘገበ ነዉ- አቶ የሺዋስ ዓለሙ


የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በ2018 ዓ/ም የክልሉ መንግስት ስድስት ወራት አፈጻጸም ላይ የሚዲያ መግለጫ ሰጥተዋል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ በመግለጫቸው እንዳመለከቱት፥ በዝግጅት ምዕራፍ ተግባርንና ተልዕኮን መሠረት ያደረገ የአመራር ስምረት በመስጠት እና በጠንካራ የተግባር ቅንጅት ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን ተችሏል ብለዋል።
ክልሉ ባለፋት ስድስት ወራት በዋና ዋና የልማት አመላካች ግቦች ውጤታማ ተግባር መፈጸሙን የገለጹት አቶ የሺዋስ፥ እየተሰሩ ባሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ህዝብ ጋር መግባባት መፈጠሩን ተናግረዋል።
በክልሉ ግብርና ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን ያመለከቱት አቶ የሺዋስ፥ በዚህ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ስነጻጸር በማሳ ሽፋንና ምርትና ምርታማነት ላይ ጭማሪ መመዝገቡን ተናግረዋል።በስድስት ወራት ዉስጥ ከ 20 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን ገልጸዋል።
የሌማት ትሩፋት በማጠናከር በከተሞች የኑሮ ውድነት ለመቋቋም የሚስችል ሥራዎች መኾናቸውን ያመለከቱት ኃላፊው፥ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በማስፋት ውጤታማነት ማሳደግ ይገባል ብለዋል።
የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ምርታማነትን በማሳደግ ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርበውን ምርት ለማሳደግ በተሰጠው ትኩረት ውጤት መመዝገቡን የጠቆሙት አቶ የሺዋስ፥ በክልሉ ሻይን በፓኬጅ የማስፋት ሥራ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
በበጀት ዓመቱ ከ15ሺህ በላይ ዜጎችን በዘላቂነት ከተረጂነት በማላቀቅ ምርታማ እንዲኾኑ ማድረግ መቻሉን የገለጹት ኃላፊው፥ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም የመሸፈን ቅድመ ዝግጅት ሥራ በሁሉም የክልሉ አከባቢ በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በግማሽ ዓመቱ ብቻ ለ24ሺህ 210 ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፈጠር መቻሉን በመጠቆም፣ በየደረጃው ለዘርፉ ሰፊ ትኩረት ተሰጥተው እየተሰራ መኾኑን ተናግረዋል።
ነጻ የምርት ዝውውር በመግታት የመልካም አስተዳደር ችግር ስፈጥሩ በነበሩ 31 ህገወጥ ኬላዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የገለጹት አቶ የሺዋስ፥ 2.2 ቢሊዮን ካፒታል ያስመዘገቡ 52 የተለያዩ ፕሮጀክቶች ፍቃድ አግኝተው ወደ ሥራ መግባታቸውን አስታውቀዋል።
በጠንካራ የአስተምህሮት፣ የህግ ማስከበር ስራና አዳዲስ ህጎችን በማውጣት በክልሉ ምሥረታ ወቅት ከ2 ቢሊዮን ያልዘለለው የክልሉ ገቢ፣ 18.4 ቢሊዮን መደረሱን በመጠቆም በበጀት ዓመቱ ድስት ወራት ብቻ ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ተናግረዋል።
በክልሉ በመሠረተ ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ላይ የኅብረተሰብ ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱንና ለዚህም የክልሉ መንግስት ያመስግናል ያሉት አቶ የሺዋስ ነባር ፕሮጀክቶችን ቀድሞ የማጠናቀቅ ሥራ በትኩረት እየተሰራ መኾኑን ገልጸዋል።
በክልሉ 20 ንጹህ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክቶች በ534 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በጀት በመንግስትና በአጋር አካለት ቅንጅት እየተሰሩ ሲሆን ባለፉት ስድስት ወራት ዉስጥ 23ሺ ህብረተሰብ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።
በስድስት ወራት ዉስጥ 255 ነጥብ 5 ኪ.ግ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መቅረቡን ገልጸዋል።
806 ሺ ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙ ሲሆን በትምህርት ለትዉልድ ፕሮግራም 392 ሚሊየን ብር ተሰብሰቦ የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል ።
በተሰራዉ የተቀናጀ ሥራ በወባ በሽታ የመያዝ ምጣኔ በ 29 .5 በመቶ መቀነሱን የጠቀሱት ኃላፊዉ፤የማህበረሰብ ጤና መድህን ሥራም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።
የከተማና የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራዎች በክልሉ ሁሉም አከባቢዎች በትኩረት እየተሰሩ ስለመኾናቸው የተናገሩት አቶ ዬሺዋስ፥ በብልጽግና ፓርቲ የወረዱ የኢንሼቲቭ ሥራዎች በአመራር ቁርጠኝነት በየደረጃው እየተፈጸሙ ነው ብለዋል።
የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያስችል የማኅበራዊ ልማት ሥራ በተሻለ መልኩ መከናወኑን ያነሱት አቶ የሺዋስ፥ የተገኙ አዎንታዊ ለውጦች ቀጣይነት ባለው መልኩ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።
በከተሞች የመልካም አስተዳደርና የአግልግሎት አሰጣጥ ችግር ምንጮችን ለማድረቅ እየተከናወኑ ያሉ የመሶብ አንድ ማዕከል፣ የከንቲባ ችሎት እና የዲጂታል አገልግሎት ሥራዎች ውጤታማ በመኾናቸው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል በመግለጫቸው አቶ ዬሺዋስ።
በቀጣይም የአመራር ቁርጠኝነትና የተግባር ቅንጅት በማጠናከር እንዲሁም የኅብረተሰብ ተሳትፎውን በማሳደግ የተጀማመሩ መደበኛና የንቅናቄ አጀንዳዎች አፈጻጸም ማላቅ እንደሚገባም ኃላፊው አስገንዝበዋል።
በዕድገቱ በዛብህ
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
በሊንክደን
https://www.linkedin.com/company/southwest-communications
በትሬድስ
https://www.threads.com/@southwest_communications
በብሉ ስካይ
