
በተያዘው በጀት ዓመት ከኢንዱስትሪው ዘርፍ የ12.8 በመቶ ዕድገት እንደሚጠበቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት 3 ዓመታት በ”ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ የተሰሩ ሥራዎች ለዘርፉ መነቃቃት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡
ምርታማነትን ለማሳደግ በአምራች ዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶችን በዘላቂነት ለመፍታት መንግሥት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ በጨርቃ ጨርቅ፣ በምግብ እና መጠጥ፣ በኮንስትራክሽን፣ በኬሚካል እና በሌሎች ዘርፎች 72 ትላልቅ ፕሮጀክቶች ገበያውን እንደሚቀላቀሉም አመላክተዋል፡፡
