

በአፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ ይህ አዲስ የሚገነባው የአውሮፕላን ማረፊያም በዓመት ከ100 አስከ 130 ሚሊዮን መንገደኞችን ያስተነናግዳል፡፡ አሁን ላይ 124 አዳዲስ አውሮፕላኖችን ለማግዛት አዘናል፡፡ ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በአፍሪካ ትልቁ የአውሮፕላን ባለቤት ብቻ ሳይሆን ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ያለው ተቋም ያደርገዋል፡፡ ይህ ለውጥ በተለይ በአገልግሎት ዘርፍ ለማስመዝገብ የተያዘውን ውስጥ ለማሳካት ሚናው የጎላ ነው፡፡ በተያዘው በጀት ዓመትም የአገልግሎት ዘርፉ 7 ነጥብ 1 በመቶ እድገት እንደሚያስመዘግብ ይጠበቃል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ
