
የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ ገቢ በሚቀጥሉት ዓመታት 50 እና 100 ቢሊዮን ዶላር ማድረስ አለብን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከሕዝብ እንደራሴዎች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡
ጠቅላይ ማኒስትሩ በማብራሪያቸው ባለፉት ሶስት ወራት ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን አስታውቀዋል፡፡
እንደጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ በሩብ ዓመቱ ያገኘነውን የወጪ ንግድ ገቢ ማስቀጠል ከቻልን በዓመት ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ልናስገኝ እንችላለን፡፡
የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ ገቢ በሚቀጥሉት ዓመታት 50 እና 100 ቢሊዮን ዶላር ማድረስ አለብን ሲሉ ተናገሩ፡፡
ኢትዮጵያ ከነበረችበት የወጪ ንግድ ገቢ የተሸሻለች ቢሆንም መድረስ ካለባት ግብ አልደረሰችም ብለዋል፡፡
