ትምህርት ቤቶች የውስጥ ገቢን ማሳደግ ለትምህርት ጥራት ያለው አስተዋጽኦ የላቀ ነዉ። አቶ አልማው ዘውዴ

Spread the love

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ትምህርት ቤቶች የውስጥ ገቢን ማሳደግ ለትምህርት ጥራት ያለው አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑን ገልጸዋል ።

በ2016 ዓ/ም በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር በጨታ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በበልግ እርሻ 141 ነጥብ 5 ኩንታል የበቆሎ ሰብል ምርት መገኘት መቻሉን ገልጸዋል።

የተገኘውን የበቆሎ ሰብል የትምህርት ቤቱን የውስጥ ገቢ ለማሳደግ በ230 ሺህ 377 ብር ተሽጦ የዉስጥ ገቢ አቅም ማሳደግ ተችሏል ብለዋል።

ሌሎች ትምህርት ቤቶችም ይህን ተሞክሮ በማስፋት የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል እንደሚገባቸውም አቶ አልማው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *