በመሬት አያያዝና አስተዳደር የአየር ንብረት ማሻሻያ (CALM) ፕሮግራም በክልሉ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ውጤታማ እንደሆነ ተገለጸ።

Spread the love

በክልሉ ግብርና ቢሮ ስር በመሬት አያያዝና አስተዳደር የአየር ንብረት ማሻሻያ መርሀግብር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ላይ የመስክ ምልከታ ተካሂዷል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮው ክፍተኛ ባለሙያዎችና የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች እንዲሁም የቴክንክ ኮሚቴዎች በመሬት አያያዝና አስተዳደር የአየር ንብረት ማሻሻያ (CALM) ፕሮግራም በዳውሮ፣ በኮንታ እና በካፋ ዞኖች በንዑስ ተፋሰስ አስተዳደርና ልማት እና የገጠር መሬት ምዝገባና አስተዳደር ስራዎችን ጎብኝቷል።

በፕሮግራሙ ትግበራ ወቅት የሴቶችና የአካል ጉዳተኞች እንዲሁም ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የገለጹት በቢሮው የተፈጥሮ ሀብት ልማትና አነስተኛ መስኖ ዳይሬክተርና የፕሮግራሙ የንዑስ ተፋሰስ አስተዳደርና ልማት አስባባሪ አቶ ተረፈ ማሞ በፕሮግራሙ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ውጤታማ መሆኑን ተናግሯል።

ተግባሩን ለመከታተል የተቋቋመው ኮሚቴ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር በየደረጃው ከሚገኘው የግብርና መዋቅሮች ጋር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በክልሉ ሁለት ወረዳዎች የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀምን ለማዘመን የምዝገባ ስራ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት
በቢሮው የመሬት አስተዳደር ዘርፍ ባለሙያና የፕሮግራሙ የገጠር መሬት ምዝገባና አስተዳደር አስተባባሪ አቶ አበበ ታደሰ ምዝገባው ስጠናቀቅ ለባለይዞታዎች ካርታና ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እንደሚሰጥ ተናግሯል።

የምዝገባው ስርዓቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው የመሬት መመዝገቢያ ቋት እየተከናወነ ሲሆን ፕሮግራሙ በአለም ባንክ የገንዘብ ድርጅት ድጋፍ እየተከናወነ እንደሆነ ነው የተገለጸው።

በመሬት አያያዝና አስተዳደር የአየር ንብረት ማሻሻያ መርሀግብር በንዑስ ተፋሰስ አስተዳደርና ልማት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ እንዲሁም የኑሮ ማሻሻያ ተግባራት በተሻለ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ እንደሚገኙም ነው በመስክ ምልከታው የተነሳው።

አርሶአደር ኡራሼ ኡታሎ እና ወ/ሮ ፀሀይ ወጫፎ በንዑስ ተፋሰስ ልማት መሠረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረው የተራቆተ አከባቢን ማልማታቸውን ገልጸዋል።

የመሬት ምዝገባው ይዞታቸውን በተገቢው እንዲለዩ እንዳስቻላቸው የገለጹት በዳውሮ ዞን የቶጫ ወረዳ አርሶአደር ደምሴ ደነፎ አሰራሩ የይዞታ ግጭት እንደሚያስቀር እምነት እንዳላቸው ተናግሯል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *