ምክር ቤቱ የቀረቡለትን የዳኞች ሹመቶችን አጽድቋል፡፡

Spread the love

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቆጭቶ ገ/ማሪያም በፍርድ ቤቱ በምልመላና መረጣ ሂደት መሰረት መስፈርትና መረጃዎችን ያሟሉ 46 ዕጩ ዳኞችን ለምክር ቤቱ እንዲሾሙ አቅርበዋል ፡፡

በቀረበው የዳኞች ሹመት

1.ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት 8፣

2.ለከፍተኛ ፍርድቤት 11፣

3.ለወረዳና ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤቶች 27 በድምሩ 46 ዕጩ ዳኞች በፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ዳኞች ሆነው እንዲሾሙ ቀርበዋል ፡፡

የቀረበውን የፍርድ ቤቶች ዳኞች ሹመት የምክር ቤት አባላት አስተያየቶችን በመስጠት በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል ፡፡

ተሿሚ ዳኞች የተሰጣቸውን ኃላፊነት ህግና አሰራርን ተከትለው በታማኝነት ለማገልገል በምክር ቤት አባላት ፊት ቆመው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል ፡፡

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *