ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሮም ጣልያን እየተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ የልማት እና የፍልሰት ኮንፈረንስ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ካላት ስትራቴጂካዊ አቅም አንጻር የስደት ምንጭ፣መሸጋገሪያ እና መድረሻ ነች። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ የስደት አስተዳደርን ለማጎልበት፣ ሕገ ወጥ ስደትን እና ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመፍታት በርካታ የፖሊሲ፣ የሕግ እና ተቋማዊ ርምጃዎችን ወስዳለች። መረጃው ከጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት የፌስቡክ ገፅ የተገኘ ነው። በተጨማሪም ሌሎች መረጃዎችን በተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ይከታተላሉ

Read More

ፕሬዚዳንት ፑቲን የአፍሪካ የሰላም ሐሳብ ለሩሲያ-ዩክሬን ሰላም መሰረት ሊሆን ይችላል አሉ

ፕሬዚዳንት ፑቲን በአፍሪካ መሪዎች የቀረበው የሰላም ሐሳብ በሩሲያ-ዩክሬን የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም የሰላም መሰረት ሊሆን እንደሚችል ገለጹ፡፡ ሬውተርስን ጠቅሶ አልጄዚራ እንደዘገበው የአፍሪካ መሪዎች ያቀረቡት የሰላም ዕቅድ ምንም እንኳን ሙሉ ዝርዝሩ ይፋ ባይደረግም ግጭቱን ለማርገብ ተከታታይ እርምጃዎችን ያመላከተ ነው፡፡ ከእነዚህም መካከል÷ የሩሲያ ጦር ወደኋላ መመለስ፣ የሩሲያ ታክቲካዊ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ከቤላሩስ ማስወጣት፣ የዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት…

Read More

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በ3 ሺህ 943 መዛግብቶች ላይ ቅጣት ማሰጠት ተችሏል–የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ

በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት በፍርድ ቤት ክርክር ከተደረገባቸው የወንጀል መዛግብቶች ውስጥ 3 ሺህ 943 መዛግብቶች ላይ ቅጣት ማሰጠት መቻሉን የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው የ2015 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የእውቅና መድረክ አካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የፍትህ ስርዓቱን ለማሻሻል በርካታ የሪፎርም ስራዎች ተከናውነዋል።…

Read More