በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በ3 ሺህ 943 መዛግብቶች ላይ ቅጣት ማሰጠት ተችሏል–የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ

Spread the love

በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት በፍርድ ቤት ክርክር ከተደረገባቸው የወንጀል መዛግብቶች ውስጥ 3 ሺህ 943 መዛግብቶች ላይ ቅጣት ማሰጠት መቻሉን የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው የ2015 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የእውቅና መድረክ አካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የፍትህ ስርዓቱን ለማሻሻል በርካታ የሪፎርም ስራዎች ተከናውነዋል።

በፍትሐ ብሔር ዘርፍ ከ7 ሺህ 400 በላይ መዝገቦች ለክርክር መቅረባቸውን ገልጸው፤ 2 ሺህ 497 በአቃቤ ሕግ ደረጃ ውሳኔ የተሰጠባቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ከእነዚህም 2 ሺህ 266 የሚሆኑትን መርታት መቻሉን እና በእዚህም መንግስት ሊከፍል የነበረውን ከሁለት ቢልዮን ብር በላይ ማዳን መቻሉን ተናግረዋል።

መንግስት የሚያከናውናቸውን ልማቶች መነሻ በማድረግ የቀረቡ እግዶችን በሚመለከትም 1 ሺህ 579 እግዶችን በማስነሳት የልማት ስራዎች እንዳይስተጓጎሉ መደረጉን አንስተዋል።

ከወንጀል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ 13 ሺህ መዛግብቶች መቅረባቸውን ገልጸው በእነዚህም የተለያየ ውሳኔ መሰጠቱን ተናግረዋል።

የፍርድ ቤት ክርክር ከተደረገባቸው የወንጀል መዛግብቶች ውስጥ 3 ሺህ 943ቱ ላይ ቅጣት ማሰጠት መቻሉን አመላክተዋል።

ባለፈው በጀት ዓመት የታዩ መልካም አፈጻጸሞችን በማጠናከር በቀጣይ ለላቀ ስኬት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የዘርፉን የሪፎርም ስራዎች በማጠናከር ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን ቅሬታዎች ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ተቋማዊ ቅንጅትን ማጠናከር እንደሚገባ አመላክተዋል ያለው ኢዜአ ነው።

በተጨማሪም ሌሎች መረጃዎችን በተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ይከታተላሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *