

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ የዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮግራም በካፋ ዞን የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ምዝገባ ማረጋገጫ ደብተር ሰጠ።
በዞኑ ጨና ወረዳ ቦባ ቆጫ ቀበሌ በፕሮግራሙ በሁለተኛ ዙር በካርታ የተደገፈ የገጠር መሬት የይዞታ ማረጋገጫ ለ389 ባለ ይዞታዎች ዛሬ ተሰጥቷል።
በመርሃግብሩ በክብር እንግድነት የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በክልሉ 87 ሺህ ቁርሽ መሬት ልኮሽ መደረጉን ገልጸው ከዚህም ውስጥ 45ሺህ የሚጠጉ ቁራሽ መሬት በዘላቂ መሬት አያያዝ መከናወኑን ተናግረዋል።
አቶ ማስረሻ አክለው የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠቱ ፋይዳው ለአርሶአደሮች የባለቤትነት ስሜት እንዲሰማቸው የሚያደርግና አለፍ ስልም ከተለያዩ አበዳሪ ተቋማት የብድር ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
ዘላቂ የመሬት አያያዝ ፕሮግራም በክልሉ በ16 ወረዳዎች ውስጥ ተፋሰስን መሠረት ያደረገ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ተግባራትን እያከነወነ እንደሚገኝ ያስረዱት በክልሉ የግብርና ቢሮ የዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ናርዶስ ታከለ ፕሮግራሙ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ላይ ትኩረት በማድረግ መሬትን በዘላቂነት አርሶአደሮች እንዲጠቀሙ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ፕሮግራሙ መሬት በዘላቂነት ልማት እየሰጠ እንዲቀጥል በእቅድ ዝግጅት እንዲሁም በዘመናዊ የእርሻ ማሳ ልኮሽ የመሬት ሀብት መረጃን ማደራጀት ስራ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተጠቁመዋል።
በዚህም በክልሉ በአየር ፎቶ የአርሶ አደር ማሳን በመለካትና በሀገረ አቀፍ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ቋት በማስገባት በክልሉ ግብርና ቢሮ የተዘጋጀውን ካርታና የማረጋገጫ ደብተር መስጠት መቻሉ ተገልጸዋል።
የይዞታ ማረጋገጫ መሰጠቱ ወጥ የሆነ የመሬት መረጃ ስረዓትን ለማደራጀት የጎላ ድርሻ እንዳለው የገለጸዉ የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንደሻዉ ከበደ ናቸዉ።
አርሶአደሮች የእርሻ ጊዜያቸውን በማሳቸው እንዲያሳልፉና ምርትና ምርታማነት እንዲያሳድጉ ያስችላል የተባለው የይዞታ ማረጋገጫ በክልሉ አምስት ወረዳዎች በዘላቂ መሬት አያያዝ ፕርግራም እየተከናወነ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
የክልል፣ የዞን የወረዳ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት የ7 መቶ 9 የመሬት ማረጋገጫ ደብተር ለአርሶአደሮች ተሰጥቷል።
