በቀረበው የአስፈጻሚ ተቋማት ሪፖርት ላይ የምክርቤት አባላት አስተያየትና ጥያቄዎችን አንስተዋል ፡፡
በተገባደደው በጀት ዓመት በክልሉ መንግስት ታቅደው የተከናወኑ ተግባራት የሚበረታቱ መሆናቸውን የምክርቤት አባላት አስተያየት ሰጥተዋል ፡፡ በክልሉ የተሻለ ኢንቨስትመንት ፍሰት የመኖሩን ያህል በዘርፋ የተሰማሩ ባለሀብቶች ኢንቨስትመንቱ ባለበት አካባቢ ምን አስተዋጽኦ አበርክተዋል የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል ፡፡ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ አንጻር የሚስተዋለውን የበቆሎ ምርጥ ዘር አቅርበት ዕጥረትን ከመቅረፍ አንጻርና አሲዳማ አፈርን ከማከም አንጻር አሁንም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ…
