በጤናው ዘርፍ ያሉ ተግባራትን ለህብረተሰቡ ለማድረስና ዘርፉን ለማሳደግ የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ

Spread the love

የወባ በሽታን መከላከልና መቆጣጠር አተገባበርን ለማሻሻል የስርዓተ ምግብ ችግር ያለባቸው እናቶች እና ህፃናት ልየታ እንዲሁም MPOX በሽታን መከላከልን አስመልክቶ ከሚዲያ አካላት ጋር የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በታጫ እየተካሄደ ነው።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ዘርፍ ባለሙያዎች ስለጤና ጉዳይ ትክክለኛ ዕውቀት በመጨበጥ ወቅታዊና ታኣማንነት ያለውን መረጃ በጊዜ ለህብረተሰቡ ለማድረስ መድረኩ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል ።

ጤና ለሁሉም መሠረት እንደመሆኑ መጠን ዜጎች ጤናማና ምርታማ እንዲሆኑና የራሳቸውን ጤና ማምረት እንዲችሉ የጤና ማጎልበት የጤና ማጎልበትና በሽታ መከላከል ፣ ስለጤና አገልግሎት እንዲሁም ስለወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ወሳኝ በመሆኑን ጨምረው ገልጸዋል ።

በመሆኑም የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች እውነታውን በመገንዘብ በለህብረተሰቡ ጠቃሚና ተኣማን መረጃ መስጠት የተዛቡ አስተሳሰቦች ሳቢያ የሚፈጠረውን መረበሽ ለማስቀረት መረጃ በማሰባሰብና በመተንተን አዘጋጅቶ ግልፀኝነትን በመፍጠርና አስተማማኝ የመረጃ ምንጭ በመሆን ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና ታአማኒ መረጃዎችን በመስጠትና በማሰራጨት ኃላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል ።

በመጨረሻም ተቀራርቦ በመስራት የተዛቡ አመለካከት እና ያሉብንን ውስንነት በመፍታት የተሳሳቱ የጤናና ጤና ነክ መረጃዎችን እንዴት ማረም እንደደሚቻል መማርና በጤናው ዘርፍ ያሉ ተግባራትን ለህብረተሰቡ ለማድረስና ዘርፉን ለማሳደግ ያለመ የምክክርና ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በመሆኑ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነትና ቅንጅት እንደሚሻ አሳስበዋል ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ህዝብ ግንኙነት ተግባቦት ዓላማ እና ሚና በሚል የተዘጋጀ ሰነድ በቢሮው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ በአቶ ተስፋዬ አየለ ለተሳታፊዎች በመቅረብ ላይ ይገኛል ።

በጌታሁን ግርማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *