የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ካቀረቧቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች መካከል:-

Spread the love

👉በኢትዮጵያ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን በመገንባት የህዝብ ጥያቄን ለመፍታት እና የሀገሪቱን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚሰራው ስራ የሚደነቅ ነው

👉ዘላቂ የሰላም ግንባታን ከማጠናከር አንጻር ምን አቅጣጫ ተይዟል ?

👉በሀገሪቱ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት ለማቃለል መንግስት የያዘው አቅጣጫ ካለ ቢብራራ

👉7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ የተሳካ ለማድረግ የተፈጠሩ አስቻይ ሁኔተዎች ምንድናቸው እንዲሁም የምርጫውን ሂደት ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ ሀይሎችን ለመግታት ምን እየተሰራ ነው ?

👉ኢትዮጵያ የጤናው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እያስመዘገበች መሆኑ አንዱ ማሳያው የማርበርግ በሽታን በአጭር ጊዜ ውስጥ መግታት መቻሏ ነው

👉የስራ አጥነትን ጉዳይ በዘላቂነት ትኩረት ሰጥቶ ከመስራት እንዲሁም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በተገኙ ውጤቶች አፈጻጸም ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ

👉በኢትዮጵያ ከፍተኛ እድገት እየተመዘገ የሚገኝ ቢሆንም በከተሞች የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤቶች ችግር ለመቅረፍ የተያዘ እቅድ ካለ ቢገለጽ ?

👉የሀገሪቱን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለማስቆም መንግስት ምን እየሰራ ይገኛል

👉የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም አሳልፎ ለመስጠት እና ለግል የፖለቲካ ፍላጎት ለማዋል የሚሰሩ አካላትን ለመከላከል ምን እየተሰራ ነው?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *