csvdcv

Spread the love

ባለፉት ሥድስት ወራት 74 ሺህ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስቶች በኢትዮጵያ የሚገኙ ብሔራዊ ፓርኮችን ጎብኝተዋል፡፡

ከእነዚህ ጎብኝዎችም በአጠቃላይ 62 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ለፋና ዲጂታል አስታውቋል፡፡

በአጠቃላይ ከተገኘው ገቢ 49 ነጥብ 8 ሚሊየን ያህሉ ከዱር እንስሳት ፍጆታዊ አጠቃቀም (ህጋዊ አደን) መሆኑንም አስረድቷል፡፡

ከኢ-ፍጆታዊ የዱር እንስሳት አጠቃቀም ደግሞ 12 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር መገኘቱን ነው ያስታወቀው፡፡

የተሻለ የጎብኝ ቁጥር ካስተናገዱት ብሔራዊ ፓርኮች መካከል÷ ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ፣ ባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ፣ ስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ፣ አብጃታ ሻላ ሐይቆች ብሔራዊ ፓርክ እና ሌሎችም እንደሚገኙበት ተጠቅሷል፡፡

በኢትዮጵያ 27 ብሔራዊ ፓርኮች እንደሚገኙ ይወቃል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *