
“ቲካሻ ቤንጊ” ከሸኮ ብሄረሰብ ቱባ ባህላዊና ታሪካዊ ክዋኔዎች ዉስጥ አንዱ ሲሆን ከአሮጌው አመት ወደ አዲሱ ዓመት ህዝቡን፣ ቤተሰቡን፣ ልጆቹን፣ እርሻውን፣ ከብቶቹንና ቀየውን በሠላም ጠብቆ ላቆየው ፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል ነው።
በሌላ ጎኑ ለቀጣይ ዓመት በህዝባችን ላይ የሚመጣ ቸነፈር ፈጣሪ ይመልስ፣ ልጆች በሰላም ወጥተው ይግቡ፣ የተወለዱት ይደጉ፣ የተዘራው እህል ፍሬ ያፍራ፣ የተተከለው ተክል ስር ይያዝ፣ ምድሪቱ ሰላም ትሁን፣ ደኑ፣አየሩ ፣ሰማይና ምድሩ ፈጣሪ ይጠብቅልን በማለት ምስጋና የሚቀርብበት በዓል መሆኑን ጠቅሰዋል።
ህብረተሰቡን ለስራ ለማነሳሳት፣ ወጣቱን በአባቶች ምክር ለማረቅ እና በአንድነት ለሠላም ዘብ ለመቆም፣ ከጎረቤት እና አብሮ ከኖሩ ህብረተሰብ ህብረትን ለመፍጠር፣ ወደ ልማት እና ዕድገት ለመግባት የሚከበር በዓል መሆኑን አመላክተዋል።
ባህላዊ ዕሴቶቻችን የወል እውነቶቻችን፣ የአብሮነታችን መሰናሰኛ ፣የአንድነታችን ምሰሶዎች መሆናቸውን የገለጹት አቶ ፍቅሬ እንደ “ቲካሽ ቤንጊ” ያሉት ባህላዊ እሴቶቻችን ሰላምን ለማጽናት ያላቸውን ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የሰላም ዕሴትን በማስረጽ የተደመረ ዓቅማችንን ተጠቅመን ልዕልናዋ የተገነባ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመጭው ትውልድ ለማሻገር ነባር ባህላዊ ዕሴቶቻችን እርሾ ናቸው ያሉት አቶ ፍቅሬ ይህ በዓል ጥንት የሸኮ ብሔረሰብ ራሱን በራሱ ባህል፣ ቋንቋ ይመራ እና ይተዳደር የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች በዓሉ ሳይከበር ቆይቷል። ብልጽግና በማህበራዊ ፕሮግራሙ የሀገራችን ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች የራሳቸውን ቋንቋ የመጠቀምና የማሳደግ፣የራሳቸውን ባህል የመግለጽና የማሳወቅ እንዲሁም ታሪካቸውን የመጠበቅ መብታቸው እንዲረጋገጥ፣ ባህላቸውንና እሴቶቻቸውን በአደባባይ ወጥተው እንዲያከብሩ እድል መስጠቱን ገልጸዋል።
በዚህም ፓርቲያችን ብልፅግና ብዝኃ ባህሎችን አዳብሮ እና አጎልብቶ ለቀጣዩ ትውልድ ለማሸጋገርና ለዓለም ጭምር እንዲተዋወቁ ለማስቻል አበክሮ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ባህላዊ እሴቶቻችንና ማህበራዊ ፀጋዎቻችን አጠናክሮ በማስቀጠል ሀገረ መንግሥት ግንባታን በማሳለጥ ሁለንተናዊ ብልፅግናን እናበስራለን ስሉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።
