

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው ጋዜጠኛ ወይም ፖለቲከኛ ስለሆነ አይታሰርም፡፡ ወደ ፊትም አይታሰርም የፖለቲካ አውዱ ሊሰፋ ይገባል፡፡
በሰዎች መታሰር ኢትዮጵያ ምንም ትርፍ አታገኝም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ግን ደግሞ ህግ መከበርና የህግ የበላይነት መከበር አለበት ብለዋል፡፡
ስልጣን ካልሰጣችሁን፣ ስንታሰር ካልፈታችሁን ምን ዲሞክራሲ አለ ከተባለ እንደዚህ አይነት ዲሞክራሲ ዓለም ላይ እንደሌለ ጠቅሰዋል።
ለሰዎች ምህረት ማድረግ ተገቢ መሆኑን በመጥቀስ፤ መንግስት የግል ጉዳይ እና ቂመኝነት የሌለበት በመሆኑ ይቅር እንላለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ለጋራ ጥቅም ሲባል በህግ መጠየቅ ያለበትን በህግ እንጠይቃለን እንጂ ግለሰቦች በመታሰራቸው የሚገኝ ፋይዳ የለም ብለዋል፡፡
