
የፕሪቶሪያ ስምምንት ለትግራይ ህዝብ እፎይታ አምጥቷል። የትግራይ ህዝብ ልጆቹን በየቀኑ ከማጣት ታድጓል። ለኢትዮጵያ ህዝብና ለሌሎች ሀገራት ደግሞ መንግስት ሰላም ይሻላል ብሎ ለተዋጉት ኃይሎች እድል ይሰጣል የሚል አዲስ ባህል ፈጥሯል። በክልሉ አገልግሎትን በሚመለከት ቴሌኮም፣ ባንኮች፣ አየር መንገድና ሌሎችም አገልግሎቶች ሙሉ ለሙሉ ጀምረዋል።
የተፈናቀሉ ሰዎችን በመሚመለከት ራያ መቶ በመቶ ጸለምትም ተመልሰዋል። ቀሪ ወልቃይት ያልተመለሱ አሉ፤ መንግስት ያልምተመለሱ ተፋናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የጸና አቋም ነው ያለው። የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ማቋቋምና ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀልም በፍጥነት መፈጸም አለበት።
ይህ ጥቅሙ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጭምር ነው። የፌደራል መንግስት ትግራይ ክልል ውስጥ ያሉ ጉዳዮችን በሰላም የመፍታት ፅኑ አቋሙን በተደጋጋሚ አሳይቷል። የትግራይ ህዝብ ጦርነት ፈጽሞ አይፈልግም። ሆኖም የዓለምን ሁኔታና የዘመኑን ውጊያ ባለመገንዘብ፣ መንግስት በተለለያዩ ችግሮች ተወሯል፤ የሚያገዙን ሀገራት አሉ በሚል የተሳሳተ ስሌት ጊዜው አሁን ነው በሚል ውጊያ ለመክፈት የሚፈልጉ አሉ። ይህ የተሳሳተ አካሄድ ነው ትግራይ የሚያስፈልገው ሰላም፣ ችገሮችን በውይይት በንግግር መፍታት ነው።
የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ ወደ ጦርነት እንዳይገባ አሁኑኑ የሰላም ሚናችሁን ተወጡ። መንግስት አንድም ጥይት የመተኮስ ፍላጎት የለውም።
ማልመት ነው ፍላጎታችን። ሁሉም ህዝብ ማወቅ ያለበት ጦርነት አያስፈልግም። ትግራይ ክልልን ጨምሮ ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬት ሁሉም የበኩሉን ሚና ማበርከት አስፈላጊ ነው።
