


በኮንፈረንስ ቱሪዝም በዓለም ላይ ስሟን የተከለችው አዲስ አበባ እንግዶቿን በድምቀት ተቀብላ ለማስተናገድ ተዘጋጅታለች ሲሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ገለፁ፡፡
ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፤ አዲስ አበባ በዚህ ወር ከምታስተናግዳቸው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች መካከል አንዱ የሆነው “ከርሃብ ነፃ አለም” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ጉባኤ ነገ እንደሚጀምር ገልፀዋል።
በአዲስ አበባ በዓድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ ከጥቅምት 26 እስከ 28 የሃገራት እና አለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የፈጠራ ባለሙያዎችና የዘርፉ ባለሙያዎች ከርሃብ ነፃ ዓለምን ስለመፍጠርና ስለዘላቂ ከባቢያዊ ልማት ይመክራሉ ብለዋል።
በኮንፈረንስ ቱሪዝም በአለም ላይ ስሟን የተከለችው አዲስ አበባም እንግዶቿን በድምቀት ተቀብላ ለማስተናገድ ተዘጋጅታለች ሲሉም ገልፀዋል።
