በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የቅመማ ቅመም ሰብሎች ሽፋን በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት ከ86 ሺህ ሄክታር መሆኑ ነው የክልሉ የግብርና ቢሮ መረጃ የሚያመለክተው።
እንደ መረጃው በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት ብቻ 418.6 ቶን የቅመማ ቅመም ምርት ወደ ማዕከላዊ ገበያ ቀርቧል።
በክልሉ መዓዛማና መድኃኒት ያላቸው ቅመማ ቅመም በስፋት ከሚመረትባቸው አከባቢዎች አንዱ ደግሞ የሸካ ዞን ነው።